አልማዝ አያና እና ሞ ፋራህ ለዓመቱ ምርጥ አትሌት የመጨረሻው ደረጃ ተፋላሚዎች መካከል ናቸው – Athlete Almaz Ayana And Mofarah

                                                                             

የዓመቱ የዓለም ምርጥ አትሌት ምርጫ 18 ቀናት ያህል ሲቀሩት በሴቶች ኢትዮጵያዊቷ አልማዝ አያና በወንዶች ደግሞ እንግሊዛዊው ሞ ፋራህ የመጨረሻው ደረጃ ላይ መድረሳቸው ታውቋል።

ግሪካዊቷ ኤካትሪኒ ስቴፋኒዲ እና ቤልጄማዊቷ ናፊሳቶ ቲያም የአልማዝ ተፎካካሪ ሆነው ሲቀርቡ ሙታዝ ኢሳ ባርሺም ከኳታር እንዲሁም ዌይድ ቫን ኒከርክ ከደቡብ አፍሪካ ከሞ ፋራህ ጋር የሚፎካከሩ አትሌቶች መሆናቸውን የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማሕበር አስታውቋል።

የ5 እና 10 ሺህ ሜትሮች ሯጯ አልማዝ ዘንድሮ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና በ10 ሺህ ሜትር አንደኛ ስትወጣ፤ በ5 ሺህ ሜትር ሁለተኛ በመውጣት ተሸላሚ መሆኗ ይታዋሳል።

አልማዝ ያለፈው ዓመት የሴቶች የዓመቱ ምርጥ አትሌት ውድድር አሸናፊ ነበረች።

                                                                             

በሌላ በኩል በወንዶቹ የለንደን የ10 ሺህ ሜትር አሸናፊ ትውለደ ሶማሊያ እና የእንግሊዝ ዜግነት ያለው ሞ ፋራህ ከኒከርክና ባርሺም ጋር ተናንቋል።

የ34 ዓመቱ ፋራህ ከትራክ ውድድር ራሱን አግልሎ አሁን ላይ ወደ ማራቶን ማድላቱ ተነግሯል።

አሸናፊዎቹ ኅዳር 15/2010 በሞናኮ በሚደረግ ዝግጅት ይፋ እንደሚደረጉ ታውቋል::

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement