የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ ከውጪ ሃገር ባስገባው የልብ ህክምና ማሽን ከመስከረም 8 ወዲህ ብዛት ያላቸው ህሙማንን ማከሙን ተናገረ፡፡

                                                                

ወንድሙ ኃይሉ

የህክምና ኮሌጁ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ነዋይ ፀጋዬ ዛሬ ለሸገር ሲናገሩ በ120 ሚሊየን ብር ወጪ ከውጪ በተገዛው የልብ ህክምና ማሽን በሚሊኒየም የጤና ኮሌጅ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የመጡ ብዙ ሰዎች የልብ ህክምና አግኝተውበታል ብለዋል፡፡

ይህ ዘመናዊ የልብ ህክምና ማሽን ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የጤና ህክምና ኮሌጅ በተጨማሪ በጥቁር አንበሣና በመቐሌ ሀይደር ሆስፒታል ብቻ እንደሚገኝ ሰምተናል፡፡

የህሙማኑን ብዛት ከግምት በማስገባት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የልብና የካንሰር ማዕከል ግንባታም እየተፋጠነ እንደሆነ አቶ ነዋይ ነግረውናል፡፡

ምንጭ:- የሸገር FM 102.1 ሬዲዮ

Advertisement