የአውስትራሊያ ፍርድ ቤት የአገሪቱን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በርናቢ ጆይስ እና የሌሎች አራት ፖለቲከኞች ሁለት ዜግነት የያዙ በመሆኑ ስልጣናቸውን ነጠቀ።
ፍርድ ቤቱ ፖለቲከኞቹ በስህተት ነው የተመረጡት ብሏል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ በስልጣን ላይ ያሉ ሶስት ፖለቲከኞች ሀላፊነታቸውን የሚለቀቁ ሲሆን፥ ቀሪዎቹ ቀደም ብለው ባለፈው የፈረንጆቹ ሀምሌ ወር ላይ ስልጣን ለቀዋል።
የሀገሪቱ ህገ መንግስት ሁለት ዜግነት ያላቸው ሰዎች መመረጥ እንደማይችሉ ያስቀምጣል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአውስትራሊያ በተጨማሪ የኒው ዚላንድ ዜግነት አላቸው በሚል ነው ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ያሳለፈው።
የፍርድ ቤቱን ውሳኔ የተቀበሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአውስትራሊያን ዜግነት ብቻ በመያዝ ዳግም ለመመረጥ እንደሚወዳደሩ አስታውቀዋል።
ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)