ትዕግስት ዘሪሁን
በቅርቡ የሥራ መልቀቂያ ያቀረቡት በሚኒስትር ማዕረግ የፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ በረከት ስምኦን ጥያቄያቸው በመንግሥት ተቀባይነት ማግኘቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ተናገሩ፡፡
በተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ በአባዱላ ገመዳ የሥራ መልቀቂያ ጉዳይ ግን እስካሁን ውይይት እየተደረገና ውጤቱም ገና መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰምተናል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ዛሬ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ተገኝተው ከአባላቱ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ ነው፡፡
አቶ በረከት የሥራ መልቀቂያ ጥያቄ ሲያቀርቡ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ ሥራ ለመልቀቅ አመልክተው እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
ይሁንና ጊዜው እንዳልሆነ ተነግሯቸውና ትግላቸውንም እንዲቀጥሉ በተደረገ ማግባባት እስካሁን ቆይተዋል ብለዋል፡፡
አሁን ግን ከመንግሥት የሥራ ኃላፊነት መልቀቅ አለብኝ የሚል አቋም በመያዛቸው ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቷል ብለዋል፡፡
ምንጭ:- የሸገር FM 102.1 ሬዲዮ