በሰከንዶች ጊዜ ውስጥ ሀይል የሚሞላው የስማርት ስልክ ባትሪ – Smartphone Battery That Can be Charged in Five Seconds

                                                  

ስማርት ስልኮች ሁሉም በሚባል ደረጃ በጣም የተሻለ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ቢሆንም ከባትሪ ጋር ተያይዞ ግን ችግር ይስተዋልባቸዋል።

በብዛት “ሊትየም አየን” የሚጠቀሙት የስማርት ስልክ ባትሪዎችን ሙሉ በሙሉ ሀይል ለመሙላት በሰዓታት የሚቆጠሩ ጊዜን ይወስዳሉ።

የካናዳ ወተርሉ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች አዲስ የሞባይል ስልክ ባትሪ ቴክኖሎጂ ይዘው መምጣታቸው እየተነገረ ነው።

አዲሱ የባትሪ ቴክኖሎጂ ሀይል የመያዝ አቅም አሁን በጥቅም ላይ እየዋሉ ካሉ ባትሪዎች ጋር ተመጣጣኝ ሲሆን፥ ሀይል የሚሞላበት ፍጥነት ግን በእጅጉ የተሻለ መሆኑ ነው የተነገረው።

ይህም አሁን በጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉት ሙሉ በሙሉ ሀይል ለመሙላት ይወስድባቸው የነበረውን የሰዓታት ጊዜ የሚቀንስ ነው ተብሏል።

ይህም አዲሱ ባትሪ በሰኮንዶች ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ እንደሚሞላ ነው የተነገረው።

አዲሱ ባትሪ ላይ የማሻሻያ ስራዎች እየተሰሩ ነው የተባለ ሲሆን፥ በቅርቡም ጥቅም ላይ መዋል አንደሚጀምር ተመራማሪዎች አስታውቀዋል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement