አዲሱ የጎግል ፒክስል ስማርት ስልክ ስክሪን ላይ ችግር ማጋጠሙ ተነገረ – The New Model Google SmartPhone Screen Problem

                                                                   

አዲሱ የጎግል ስማርት ስልክ ለገበያ መቅረብ ከጀመረ ሁለት ሳምንታት ያስቆጠረ ሲሆን፥ ስክሪኑ ላይ ግን ችግር እያጋጠመ መሆኑን ነው ተጠቃሚዎች እየተናገሩ ያሉት።

ስልኩን ላለፉት ሁለት ሳምንታት የተጠቀሙ ሰዎች እንደተናገሩት፥ የስልኩ ስክሪን በውስጥ በኩል መቃጠሉን የተናገሩ ሲሆን፥ አንዳንዶች ደግሞ የስልኩ ስክሪን የተደበላለቀ እና ጭቃ የሚመስል እንደሆነባቸው ነው የተናገሩት።

ጎግል በበኩሉ ጉዳዩን ትኩረት እንደሰጠው እና ጥልቅ ምርመራ እያደረገበት እንደሚገኝ አስታውቋል።

የጎግል ፒክስል ምርቶች ምክትል ፕሬዚዳንት ማሪዮ ኩዌሪየዝ፥ የሚደርሱንን ጥቆማዎች በሙሉ በትኩረት ክትትል ይደረግበታል፤ በችግሩ መንስኤ ላይም አፋጣኝ ምርመራ ይደረጋል ነው ያሉት።

የሚደረገው ምርመራ እንደተጠናቀቀም መረጃውን ይፋ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።

ጎግል የፒክስል ስማርት ስልኩ ቤተሰብ የሆኑትን ፒክስል 2 እና ፒክስል 2 XL የተባሉ ሁለት አዳዲስ ስማርት ስልኮቹን ከሁለት ሳምንታት በፊት ነበር ይፋ ያደረገው።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement