የአፍ መድረቅ መንስኤ እና መፍትሄዎቹ | Dry Lips Treatment

የአፍ መድረቅ ችግር በአብዛኛው ጊዜያዊ ችግር እንጂ የከፋ የጤና ችግር ምልክት ሊሆን እንደሚችል አይገመትም:: ይሁን እንጂ ሰውነታችን ያለ በቂ ምክንያት በአፋችን ውስጥ እርጥበት(ምራቅ) እንዲኖር አያደርግም:: 

ለጥርስ መበስበስ ምክንያት የሚሆኑ ባክቴሪያዎች ደረቅ ሁኔታ ይመቻቸዋል ስለዚህ የአፍ መድረቅ ለጥርስ እና ሌሎች በሽታዎች ምክንያት ሊሆን ይችላል:: 
ምራቃችን የአልካላይ ይዘት ያአለው ሲሆን የምንመገባቸውን የአሲድ ይዘት ያዘት ያላቸው ምግቦች ጥርሶቻችን እንዳያበላሹት ያደርጋል::

የአፍ ድርቀት መንስኤዎች
– መድሃኒቶች
የጨጓራ እና ደም ግፊት ህመምን የአዕምሮ መቃወስን ለማከም የሚወሰዱ መድሃኒቶች የአፍ ድርቀትን ከሚያስከትሉ መካከል ያጠቀሳሉ 
– እርጅና
እድሜያች እየጨመረ ሲሄድ የምራቅ አመንጪ እጢዎች ምራቅ የማመንጨት አቅማቸው ይቀንሳል 
– የውሀ ጥም 
ሰውነታችን በቂ ውሀ ሳያገኝ ሲቀር ምራቅ የማመንጨት አቅሙ ይወርዳል 
– የአተነፋፈስ ችግር 
ከአፍ ይልቅ በአፍንጫ መተንፈስ በርካታ ጥቅሞች እንዳሉት ይነገራል:: የመተንፈሻ አካልት ችግር በተለይም የአፍንጫ ቀዳዳዎች መዘጋት ግን በአፍ ብቻ እንድንተነፍስ ያስገድዱናል በመሆኑም ለረጅም ሰአት በአፍ መተንፈስ የአፍ ድርቀት ያመጣል 
የካንሰር ህክምናዎች በጨረርም ሆነ በኬሞቴራፒ የሚደረግ የካንሰር ህክምና ለአፍ መድረቅ መንስኤ ሊሆን ይችላል

ለአፍ መድረቅ መፍትሄዎች
– ውሀ በብዛት መጠጣት;-የአልኮል መጠጥ ከጠጡ በኋላ የአፍ መድረቅ ስሜት የሚሰማቸው ሰዎች ውሃ አብዝተው መጠጣት አለባቸው በተለይም ቀይ ወይን የአፍ ውስጥ እርጥበትን የመቀነስ አቅምሙ ከፍተኛ በመሆኑ በቂ ውሃ መጠጣት ያስፈልጋል::
– የስኳር ይዘት የሌላቸውን ከረሜላዎችን እና ማስቲካዎች ማኘክ የምራቅ መመረትን ስለሚያሳድግ ይመከራል 
– የአፍ ድርቀት ለመቀነስ የተዘጋጁ የጥርስ ሳሙናዎችን መጠቀም 
ይሁን እንጅ ሁሌም ከእንቅልፍ ስንነቃ የጉሮሮ ህመም የሚሰማን ከሆነ እና ሌሎች የአፍ ድርቀት ምልክቶችን ካስተዋልን ወደ ህክምና መሄድ ያስፈልጋል:: ከዚህ በተጨማሪ የታዘዘልን መድሃኒት ለአፋችን መድረቅ ምክንያት ሆንዋል ብለን ካስብን ሀኪማችንን ማማከር ተገቢ ነው::

ምንጭ:- ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement