በ2009 ዓ.ም ለመንገድ ልማት ተነሺዎቸ ከ88 ሚሊየን ብር በላይ ካሳ ተከፍሏል – የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን – Over 88 million Birr spent for highway constructions

                                                      

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለመንገድ ልማት ተነሽዎች እና ለመሰረተ ልማት ተቋማት ከ88 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ካሳ መክፈሉን አስታወቀ።

በዚህም በራስ ሀይል የሚገነቡ 43 የመንገድ ፕሮጀክቶች፣ 27 የኮንትራት ፕሮጀክቶች እና 13 በጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚገነቡ የመንገድ ፕሮጀክቶችን በድምሩ 83 የመንገድ ፕሮጀክቶችን የወሰን ማስከበር ስራዎች መስራት መቻሉን ነው ባለስልጣኑ ያሳወቀው።

በወሰን ማስከበር በተሰራው ስራም ከ800 በላይ ቤቶችን ለማንሳት ተችሏል።

በበጀት ዓመቱም ከ1 ሺህ 500 በላይ ቤቶችን ለማንሳት ከተያዘው እቅድ አንፃር አፈፃፀሙ 53 በመቶ ነው ተብሏል።

በተጨማሪም የመሰረተ ልማት ተቋማት ጋር በተሰራ የቅንጅት ስራ ከ1 ሺህ 200 በላይ የመብራት፣ ቴሌኮም እና የውሃ መስመሮችን ለማንሳት ከተያዘው እቅድ፥ ከ800 በላይ የሚሆኑትን በማንሳት የእቅዱ 70 በመቶውን ማሳካቱን ነው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የገለፀው።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement