ዜድ ቲ ኢ ባለሁለት ስክሪን ታጣፊ ስልክ ይፋ አደረገ – ZTE reveals folding handset that can turn into a tablet

                                                                        

ዜድ ቲ ኢ አክሰን ኤም የተባለ ባለሁለት ስክሪን ታጣፊ ስማርት ስልኩን በአሜሪካ ይፋ አደረገ።

የቻይናው ግዙፍ የተንቀሳቃሽ ስልክ አምራች እና አቅራቢ ኩባንያ ዜድ ቲ ኢ አዲሱን ስልክ ማስተዋወቁ በገበያው ያለውን ተወዳዳሪነት ከፍ ያደርግለታል ተብሏል።

ስልኩ ሁለት ስክሪኖች ያሉት ሲሆን የእያንዳንዳቸው ስፋት 5 ነጥብ 2 ኢንች ነው።

እነዚህ ስክሪኖች መታጠፍ እና መዘርጋት የሚችሉ ሲሆን፥ ሲያስፈልግ እንደማንኛውም ስልክ መጠቀም የሚያስችሉ ናቸው።

አክሰን ኤም ስማርት ስልክ የተጠቃሚውን የተለያዩ ፍላጎቶች የሚያስተናግዱ ሶስት የመልዕክት ማስተላለፊያ እና የመስሪያ ክፍሎችም አሉት።

በሁለቱ ክፍሎች ተጠቃሚው የተለያዩ መተግበሪያዎችን በሁለቱ ስክሪኖች እንዲከፍት የማድረግ ስራን ያግዛሉ።

ለምሳሌ በአንደኛው ስክሪን ላይ የመልዕክት መላላኪያ መተግበሪያ ቢከፍት፥ ማለትም ፌስቡክ፣ ዋትስ አፕ ወይም ቫይበር ከፍቶ ቢጠቀም፥

በተመሳሳይ ጊዜ በሁለተኛው ስክሪን የሞባይል ጨዋታዎችን (ጌሞችን) መጠቀም ያስችላሉ ማለት ነው።

ከዚህ ውጭ ሁለቱም ስክሪኖች በአንድ ላይ በመለጠጥ ቪዲዮን በትልቁ መጠን ለማየት እና ሌሎችን ምስሎችን በግዝፈት ለማየት ይረዳሉ።

የዜድ ቲ ኢ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሌክሲን ቼንግ አዲሱ ስማርት ስልክ በቻይና፣ በአውሮፓ እና በጃፓን አገልግሎት ላይ እንደሚውል ታነግረዋል።

በመጪው ህዳር ወር የሞባይልክ አከፋፋዮች አክሰን ኤም ስልክን ለደንበኞቻቸው እንደሚያቀርቡ ተነግሯል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement