በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ ወረዳዎች በተከሰተው ግጭት የተሳተፉና ጉዳት ያደረሱ አካላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ሚኒስትር አስታወቁ፡፡
አዲስ አበባ —
በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ ወረዳዎች በተከሰተው ግጭት የተሳተፉና ጉዳት ያደረሱ አካላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ሚኒስትር አስታወቁ፡፡
በግጭቱ የተፈናቀሉት ሰዎች በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ መሆናቸውን የገለፁት ሚኒስትሩ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በተለይ መንግሥት የአሰማራው የሰብዓዊ መብት ጥሰት መርማሪ ቡድን ሪፖርት ሲጠናቀቅ ተጨማሪ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ:- ቪ ኦ ኤ(VOA)