ፌስቡክ ታዳጊ ልጆች እርስ በእርሳቸው መልካም እንዲሆኑ የሚረዳ መተግበሪያ ገዛ

                                                  

ፌስቡክ ታዳጊ ልጆች እርስ በራሳቸው መልካም አንዲሆኑ የሚረዳ አዲስ መተግበሪያ መግዛቱ ተነግሯል።

መተግበሪያው “ቲ.ቢ.ኤች (tbh)” የሚል መጠሪያ ያለው ሲሆን፥ ይህም “to be honest” ሀቀኛ ስለመሆን የሚል ትርጓሜ ያለው መሆኑም ተነግሯል።

መተግበሪያው ከተሰራ ገና የዘጠኝ ሳምንታት እድሜን ያስቆጠረ ቢሆንም፥ እስካሁን ግን ከ5 ሚሊየን በላይ ሰዎች አውርደውት ወይም ዳወንሎድ አድርገው እየተጠቀሙት እንደሆነም ተገልጿል።

የመተግበሪያው ፈጣሪዎች፥ “መተግበሪያው ካለን አቅም አንጻር ብዙ ውጤት ማምጣት አይችልም ነበር፤ አሁን ግን ለፌስቡክ ምስጋና ይድረስ እና ከፍተኛ አቅም አግኝቷል ብለዋል።

ፌስቡክ መተግበሪያውን በስንት ገዛ የሚለው ግልጽ የሆነ ነገር ባይኖርም፤ ቴክ ክራንች የተባለ የቴክኖሎጂ መረጃዎች አቅራቡ ግን ፌስቡክ ከ100 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ባነሰ ዋጋ መተግበሪያውን እንደገዛ አስታውቋል።

እንዲሁም “ቲ.ቢ.ኤች (tbh)” የተባለውን መተግበሪያ የፈጠሩ አራቱ ሰዎች የፌስቡክ ኩባንያ ሰራተኞች ሆነው እንደሚቀጠሩም ገልጿል።

ፌስቡክ ባወጣው መግለጫ፦ ቲ.ቢ.ኤች መተግበሪያ እና ፌስቡክ ሰዎች መልካም ነገሮችን እንዲሰሩ እና እርስ በእርስ እንዲቀራረቡ የሚያደርግ የጋራ አላማ ላቸው ብሏል።

ቲ.ቢ.ኤች በምልእክት መለዋወጥ ይህን ስራ መስራቱ በጣም የሚያስገርም ነው ያለው ፌስቡክ፥ ከዚህ በኋላ መተግበሪያው የፌስቡክን አቅም በመጠቀም መልካም ነገሮች መስራቱን አጠናክሮ ይቀጥላልም ብሏል።

ቲ.ቢ.ኤች በበኩሉ መተግበሪያው ስኬታማ የሆነው የኢንተርኔት ተጠቃሚ ታዳጊ ህጻናት መተግበሪያውን ለመጠቀም ያላቸው ከፍተኛ ፍላጎት ነው ብሏል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement