NEWS: የቱርክ ጦር የሶሪያን ድንበር አቋርጦ ገባ

                                                        

የቱርክ ጦር ለአዲስ ወታደራዊ ዘመቻ ወደ ሶሪያ ድንበር ዘልቆ ገባ።

በ12 ብረት ለበስ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች የተጫኑ የቱርክ ወታደሮች ወደ ሰሜናዊ ሶሪያ ኢድሊብ ማቅናታቸው ተነግሯል።

ጦሩ በኢድሊብ ምንም ዓይነት ግጭት እንዳይኖር ቱርክ ከሩሲያ እና ኢራን ጋር የገባችውን ስምምነት ለማስተግበር እንደገባ ነው የተገለፀው።

ጦሩ በአከባቢው ከግጭት ነፃ የሆነውን ቀጠና ለመቆጣጠር የሚያስችል ኬላዎችን በማቋቋም ላይ ነው።

በአከባቢው የሚገኙ ታጣቂዎች ከግጭት ለመታቀብ ይስማማሉ ወይስ መሳሪያቸውን ያስረክባሉ ለሚለው ጥያቄ መልስ የሚፈልጉ ወገኖች በሁኔታው ፍርሃት ይሰማቸዋል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement