የኢትዮጵያ ማሪታይም አካዳሚ በመርከብ ምህንድስና ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 104 ተማሪዎች አስመረቀ

                                              

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ማሪታይም አካዳሚ በመርከብ ምህንድስና ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 104 ተማሪዎች አስመርቋል።

ትላንት ለምረቃ የበቁት ሰልጣኞች ቀደም ሲል ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በመካኒካል እና ኤሌክትሪካል ኢንጅነሪንግ የተመረቁ ናቸው። 

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ባይሌ ዳምጤ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት፣ ተመራቂዎቹ ወደ ተግባራዊ ሥራው ሲሰማሩ ሙያዊ ኃላፊነታቸውን በብቃት መወጣት ይጠበቅባቸዋል።

በቆይታቸው ያገኙትን ዕውቀት እና ክህሎት በተግባር በመተርጎም በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ የኢትዮጵያን ገፅታ መገንባት እንዳለባቸውም ተነግሯል:: 

ሰልጣኞቹ በትምህርት ቆይታቸው ወቅት በዓለም አቀፍ የመርከብ ድርጅቶች ተወዳድረው ማሸነፍ የሚያስችላቸውን እውቀትና ክህሎት በንድፈ ሃሳብና በተግባር ተደግፎ እንዲያገኙ መደረጉን የገለፁት ደግሞ የአካዳሚው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚስተር አቪሻይ ማርዚያኖ ናቸው።

አካዳሚው የዛሬ ተመራቂዎችን ጨምሮ እስካሁን ድረስ ከአንድ ሺህ 200 የሚበልጡ የመርከብ ምህንድስና ተማሪዎችን አሰልጥኖ በማስመረቅ ወደሥራ ማሰማራቱን ዩኒቨርሲቲውን አስታውቋል። 

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement