NEWS: ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ የሁለቱን ምክር ቤቶች ሶስተኛ የስራ ዘመን በንግግር እየከፈቱ ነው

                                                      

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ሶስተኛ የስራ ዘመን የመክፈቻ ንግግርን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።

ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው ያለፈውን 2009 በጀት ዓመት የመንግስት አፈፃፀምን አቅርበዋል።

በንግግራቸው ኢኮኖሚው የ10 ነጥብ 9 በመቶ ማደጉን አንስተዋል።

ይህም ውጤት ኢኮኖሚው በጠንካራ ሁኔታ ማገገሙ እና ከተቀመጠው እቅድ ጋር ተቀራራቢ መሆኑን ያሳየ ነው ብለዋል።

በዓመቱ ውስጥ ግብርና የ6 ነጥብ 7 በመቶ አስተዋፅኦ ያበረከተ ሲሆን፥ ድርቁ እና የአሜሪካ መጤ አረም ተፅእኖ በኢንዱስትሪው ላይ መስተዋሉን ገልፀዋል።

የኢንዱስትሪ ዘርፍ የ18 ነጥብ 7 በመቶ እና የአግልግሎት ዘርፍ 10 ነጥብ 3 በመቶ እድገት ማሳየታቸው ነው የተጠቀሰው።

በአጠቃላይ በዓመቱ በኢኮኖሚ ውስጥ የኢኮኖሚ ሽግግር የታየበት መሆኑን ነው ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ አስታውቀዋል።

በ2010 በጀት ዓመትም የኢኮኖሚው አማካይ እድገት የ11 ነጥብ 1 በመቶ እንዲሆን መታቀዱን ያነሱት ፕሬዚዳንቱ፥ ግብርና ቢያንስ የ8 በመቶ እንዲያድግ እና የኢንዱስትሪው ዘርፍ የላቀ እድገቱን እንዲቀጥል ይደረጋል ነው ያሉት።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement