በአሜሪካ ልጄን አላስከትምብ ያለችው እናት ለእስር ተዳርጋለች

                                         

የአሜሪካዋ ሚቺጋን ነዋሪ የሆነችው እናት ልጄን አላስከትብም በማለቷ ለእስር ተዳርጋለች።

ሬቤካ በሪዶው የተባለችው እናት የዘጠኝ ዓመት ልጇን ለማስከተብ ከባለቤቷ ጋር ከተስማሙ በኋላ ባለማስከተቧ ነው ለእስር ልትዳረግ የቻለቸው።

በዚሁ ጉዳይም ፍረድ ቤት የቀረበቸው እናት የሰባት ቀናት የእስር ቅጣት የተላለፈባት ሲሆን፥ ልጁም በአስቸኳይ እንዲኪተብ ሲል ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ አስተላልፏል።

የቀድሞ ባለቤቷል ልጁን ወስዶ እንዲያስከትብም ከፍርድ ቤቱ ፈቃድ ተሰጥቶታል። 

የአሜሪካዋ ሚቺጋን ነዋሪዎች በተለያየ እምነት ምክንያት ልጆቻቸውን ማስከተብ ካልፈለጉ የሚፈቀድላቸው ቢሆንም፥ ሬቤካ በሪዶው ግን ልጇን ለማስከተብ ከቀድሞ ባለቤቷ ጋር ስምምነት ላይ ከደረሰች በኋላ ባለማስከተቧ ነው ለእስር የዳረጋት።

የሁለት ልጆች እናት የሆነችው ሬቤካ በሪዶው ልጇን ለማስከተብ የገባችውን ቃል ባለመፈፀሟ ባሳለፍነው ረቡእ ፍርድ ቤት በመቅረብ የሰባት ቀን የእስር ቅጣት ተበይኖባታል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement