NEWS: ግብፅ ከሰሜን ኮርያ የመጡቨ ፀረ-ታንክ ሚሳይሎችን ከጥቅም ውጭ አደረገች

                                                       

ግብፅ ከሰሜን ኮርያ የመጡ ፀረ-ታንክ ሚሳይሎችን ከጥቅም ውጭ ማድረጓን አስታወቀች።

የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አህመድ አቡ ዘይድ ሚሳኤሎችን ወደ ግብፅ ለመላክ የታሰበው ሙከራ አለመሳካቱን ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ ግብፅ ከሰሜን ኮርያ ሚሳኤሎችን ገዛች በሚል በዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ የወጣው ዘገባ ሀሰት ነው ብለዋል።

“ግብፅ ሰሜን ኮሪያን በተመለከተ የፀጥታው ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ ቃል አልገባችም በሚል የወጣው ሪፖርት የተሳሳተ ግንዛቤ ለመፍጠር የተሞከረ ነው” ሲሉ ቃል አቀባዩ ገልፀዋል። 

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በሰሜን ኮሪያ ያሳለፋቸው ማዕቀቦች መተግበር ላይ የግብፅን ትብብር ማወደሱን አንስተዋል። 

ግብፅን የሚሳኤሎች መድረሻ አድርጎ የወሰደው የእገዳ ኮሚቴው ሪፖርት፥ ጭነቱ ወደ ግብፅ እየሄደ እንደነበር ቢጠቅስም ቅርብ ወይም ሩቅ የሚለውን አለማመላከቱን ዘይድ ተናግረዋል። 

ሰሜን ኮሪያ የሚሳኤል ፕሮግራም መጀመሯን እና በተደጋጋሚ የኒክሌር ሙከራዎች ማካሄዷን ተከትሎ ጠንካራ ማዕቀቦች ተጥሎባታል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement