የቶንሲል ህመምን በቤት ውስጥ ለማከም

                                                                                

በጉሮሮ ግራና ቀኝ የሚገኙ ሁለት እጢዎች ሲሆኑ፥ የተለያዩ
ባክቴሪያዎችና ቫይረሶች ወደ ሰውነታችን ዘልቀው እንዳይገቡ
ይከላከላሉ።
የሰውነታችን በሽታ የመከላከል አቅም የሚያሳድጉ ነጭ የደም
ህዋሳትንም ያመርታሉ።
እነዚህ እጢዎች ራሳቸው ሲመረዙ ቶንሲሊቲስ የተሰኘ በተለምዶ
ቶንሲል ብለን የምንጠራው ህመም ይከሰታል።
በባክቴሪያ አልያም ቫይረስ ኢንፌክሽን የሚ
ከሰተው የቶንሲል
ህመም፥ የቶንሲል እጢዎችን የማሳበጥና ጉሮሮን የመከርከምልክቶች
አለው።
ህመሙ አንዳንድ ጊዜም መተንፈስ አለማስቻልን ሊያስከትል ሁሉ
ይችላል።
ቶንሲል በየትኛውም የእድሜ ክልል የሚከሰት ስሆን፥ በህፃናት እና
ታዳጊዎች ላይ ግን በጣም የተለመደ ነው።
የቶንሲል ህመም ምልክቶች
– የጉሮሮ ህመም፣
– ምግብ የመዋጥ ችግር፣
– የድምፅ ለውጥ፣
– መጥፎ አተነፋፈስ፣
– ትኩሳት፣
– የጆሮ ህመም፣
– ራስ ምታ
ት፣ ወዘተ..
የቶንሲል ህመምን የተለያዩ መድሃኒቶችን በመውሰድ መከላከል
የሚቻል ሲሆን፥ ብዙ ጊዜ በቤት ውስጥ በሚዘጋጁ ነገሮች በቀላሉ
ማከም እንደሚቻል ይታወቃል።
ውሃ ውስጥ ጨው ጨምሮ አፍን መጉመጥመጥ፣ አፍ እና ጉሮሮን
ከጎጂ ተህዋስያን ለማፅዳት እና በቶንሲል እጢዎች አካባቢ ሌላ
ኢንፌክሽን እንዳይከሰት ያግዛል።
የፍራፍሬ ጭማቂዎችን ከሶስት እስከ አምስት ቀናት መውሰድ በሽታ
የመከላከል አቅምን በማሳደግ የትኛውንም መመረዝ (ኢንፌክሽን)
ለመዋጋት ያግዛል።
ከሚጎመዝዙና ቅመማ ቅመም ከበዛባቸው ምግቦችና መጠጦች ግን
መራቅ ተገቢ ነው ተብሏል።
የቶንሲል ህመምን በቤት ውስጥ ለማከም የሚረዱ ዘዴዎች
1. ማር

 አንድ ብርጭቆ ውሃ ውስጥ አራት ማንኪያ ማር፣ ሩብ ማንኪያ ጨው
እና የሎሚ ጭማቂ ጨምረን በማዋሃድ በቀን ከ2 እስከ 3 ጊዜ
መጠጣት ጥሩ ወጤት ያስገኛል።
2. በርበሬ እና እርድ
አንድ ብርጭቆ የፈላ ወተት ላይ የእርድ ብናኝ እና ጥቂት በርበሬ
ጨምሮ በማዋሃድ ከመኝታ በፊት መጠጣት ህመሙን ያስታግሳል።
3. ካሮት፣ ቀይ ስር እና ኩከምበር
300 ግራም ካሮት፣ 100 ግራም ቀይ ስር እና 100 ግራም ኩከምበር
በአንድ ላይ በመፍጨት ጭማቂ በማዘጋጀት መጠቀምም ሌላኛው
ለህመሙ መፍትሄ ነው ተብሎ የተጠቀሰ ነው።
4. ሎሚ
አንድ ሎሚ ለሁለት በመክፈል ጨው መነስነስ፤ ከዚያም በመ
ጭመቅ
መጠጣትም ጥሩ መፍትሄ ያስገኛል ተብሏል።
5. በረዶ
ብዙዎቻችን በረዶ እንዴት የቶንሲል ህመምን ለመቅረፍ ይረዳል
የሚለው ጉዳይ ሊያስገርመን ይችላል።
ነገር ግን በረዶ ችግሩን በማስወገድ ረገድ ውጤታማ መሆኑ ነው
የሚነገረው።
የተወሰኑ የበረዶ ጡቦችን በጨርቅ ጠቅልሎ ወደ ቶንሲል እጢዎች
በመላክ ከ10 እስከ 15 ደቂቃ መቆየት፤ ይህንኑ በቀን ለአራት ጊዜ
ማከናወን ህመሙን በአጭር ጊዜ ለማስወገድ ይረዳል።
6. ዝንጅብል
ዝንጅብል ጨምቀን ሞቅ ካለ ውሃ ጋር ማዋሃድ (ካስፈለገም አንድ
ማንኪያ ማር መጨመር ይቻላ
ል)፤ ከዚያም በቀን ለአንድ ወይም ሁለት
ጊዜ መጉመጥመጥ።
ዝንጅብልን ሻይ ውስጥ ጨምሮ መጠጣትም ሌላኛው አማራጭ ነው።
7. ቀይ ሽንኩርት
ቀይ ሽንኩርት በመፍጨትና ከሞቀ ውሃ ጋር በማዋሃድ አፍን
መጉመጥመጥ ህመሙን ለማስታገስ እንደሚያግዝም ተነግሯል።
በአጠቃላይ ከላይ የተጠቀሱትን ዘዴዎች በመጠቀም ህመሙ
ሊታገስልን ካል
ቻለ ወደ ህክምና ተቋማት በመሄድ አስፈላጊውን
ምርመራ ማድረግ ተገቢ ነው።

ምንጭ:- ጤናችን

 

Advertisement