NEWS: ወጋገን ባንክ ከ805 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባውን ባለ 23 ወለል ህንጻ አስመረቀ

                                                                                   

ወጋገን ባንክ ከ805 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባውን ባለ 23 ወለል የዋና መስሪያ ቤት ህንጻ ትላንት አስመረቀ።

ህንጻውን በክብር እንግድነት ተገኘተው የመረቁት ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ፥ በርካታ የግል ባንኮች ለባለሃብቶችና የንግድ ድርጅቶች የፋይናንስ ምንጭ በመሆን ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ ነው ብለዋል።

ወጋገን ባንክም ከእነዚህ መካከል አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፥ ባንኩ በቀጣይ በኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ የልማት ዘርፎች ለተሰማሩ ባለሃብቶች ተጨማሪ የካፒታል ምንጭ በመሆን ሚናውን አጠናከሮ ሊቀጥል ይገባል ነው ያሉት።

የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተፈሪ ዘውዱ በበኩላቸው፥ ህንጻው የባንኩን ተወዳዳሪነት በማሳደግ በ2025 በአፍሪካ ከሚገኙ አስር ስመጥር እና ተፎካካሪ ባንኮች አንዱ ለመሆን ያስቀመጠውን ራዕይ ለማሳካት አቅም እንደሚፈጥር ተናግረዋል።

ህንጻው የደህንነት፣ የኤሌክትሪክ መስመሮችና የሙቀትና ቅዝቃዜ መቆጠጠሪያ እና ዘመናዊ አስተዳደር እንዳለው በምርቃት ስነ ስርዓቱ ወቅት ተገልጿል።

በ1 ሺህ 800 ስኩየር ሜትር ላይ ያረፈው ህንጻ፥ ከምድር በታች ሶስት የተሽከርካሪ ማቆሚያ ወለሎች አሉት።

ህንጻው ከመሬት በላይም 107 ሜትር እንዳለው መሆኑ ነው የተገለጸው።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement