ጣሊያናዊቷ ጎልማሳ ራሷን አግብታለች

                                                                     

የ40 አመቷ ጎልማሳ ላውራ ሜሲ ጣሊያናዊት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አሰልጣኝ ናት።

ጎልማሳዋ አሰልጣኝ የዛሬ ሁለት አመት ለ12 አመታት የዘለቀው የፍቅር ግንኙነቷ ባለመስማማት መቋጫውን አግኝቷል፤ እርሷም ከዚያ ወዲህ በብቸኝነት ቆይታለች።

አጋጣሚው በተፈጠረበት ወቅት ታዲያ ለራሷ አንድ ቃል ገብታ ነበር፤ 40 አመት እስከሚሞላኝ የህይዎት አጋር የሚሆነኝን ወንድ ካላገኘሁ ራሴንበ አገባለሁ የሚል።

የሚሆነኝ ወንድ ካገኘሁ አገባለሁ፤ የእኔ ደስታ ግን በእርሱ ላይ የተወሰነ አይደለም የሚል አመለካከቷንም ታንጸባርቃለች።

ይህን ካለች በኋላ እንዳሰበችው የህይዎት አጋሯን ሳታገኝ በመቆየቷ ከሰሞኑ መለስተኛ በሚባል ሰርግ ራሷን አግብታለች።

“ሁላችንም ቢሆን ራሳችን መውደድና ማፍቀር አለብን” የምትለው ላውራ፥ ያለ ባልም ቢሆን የሚነገር የሰርግ ታሪክ ይኖራል የሚል እምነቷን ገልጻለች።

70 ሰዎችን በጠራችበትና ራሷን ባገባችበት የሰርግ ስነ ስርዓት ላይም፥ ላውራ በሙሽራ ቬሎ ተውባና ለሰርጉ የሚያስፈልግ ኬክና መሰል እንግዳ ማስተናገጃዎችን በራሷ ወጪ ሸፍናለች።

ወይዘሮ ላውራ ራሷን በማግባትም የመጀመሪያዋ ጣሊያናዊት ሴት ሆናለች።

ከሰርጉ ስነ ስርዓት በኋላ በርካቶች በውሳኔዋ አለመደሰታቸውን በመልዕክታቸው አድርሰዋታል።

ራስን የማግባት ውሳኔው የበዛ ራስ ወዳድነትና የማይጠቅም ነው በሚልም ተችተውታል።

እርሷ ግን ማንም ሆነ ምንም አይነት ነገር ደስታየን አይቀማኝም ስትል ሃሳቧን ለኮነኑት ምላሽ ሰጥታለች።

የሃሳቡ ደጋፊዎች በበኩላቸው የላውራ ውሳኔ ራስን ከመውደድና ከማፍቀር አንጻር ብቻ ሊታይ ይገባል የሚል አቋም አላቸው።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement