NEWS: የእንግሊዙ ኩባንያ የወባ ትንኞችን የሚያጠቁ 1 ቢሊየን ትንኞችን በየሳምንቱ ሊለቅ ነው

                                              

የእንግሊዙ የባዩቴክ ኩባንያ በየወባና የዚካ አምጪ ትንኞችን የሚያጠቁ 1 ቢሊየን ትንኞችን በየሳምት ሊለቅ ነው።

የሚለቀቁት ትንኞች በየወባና የዚካ ቫይረስን እንደማያስተላልፉ የሚታወቁት ወንድ ትንኞች መሆኑንም ኩባንያው አስታውቋል።

እነዚህ ትንኞች በሚናደፉበት ጊዜ ቫይረሶችን በማስተላለፍ የሚታወቁተን ሴት የወባ እና የዚካ ትንኞችን ነው የሚከላከሉት።

ወንድ ትንኞቹ በዘረመላቸው ላይ ማስተካከያ የተደረገባቸው ሲሆን፥ ከሴቶቹ ጋር ግንኙነት በሚፈፅሙበት ጊዜ ሴት ትንኞቹ በሽታ ከማስተላለፋቸው በፊት እንዲሙቱ ያደርጋሉ።

በየሳምንቱ የሚለቀቁት 1 ቢሊየን የበሽታ ተከላካይ ወንድ ትንኞቸም በተለየም በገዳይነታቸው የሚታወቁትን ቢጫ ወባ፣ ዚካ እና መሰል በሽታዎችን ለመከላከል እንደሚረዱ ተነግሯል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

 

Advertisement