እንግሊዛዊው ብስክሌተኛ በ79 ቀናት ዓለምን በብስክሌት በመዞር አዲስ ክብረ ወሰን ያዘ

                                                          

እንግሊዛዊው ብስክሌተኛ ማርክ ቤማውንት በ80 ቀናት ውስጥ በብስክሌት ዓለምን ለመዞር ነበር ጉዞውን የጀመረው።

የ34 ዓመቱ ብስክሌተኛ ማርክ ጉዞውን ካቀደው ቀን በአንድ ቀን ቀድሞ በ79 ቀን በመግባት አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን በእጁ ማስገባቱ ነው የተነገረው።

ማርክ ከዚህ በፊት የነበረውን ክብረወሰንም በ44 ቀናት ማሻሻሉ ነው የተነገረው።

ማርክ በቀን 386 ኪሎ ሜትር እና ኪያ በላይ እየተጓዘ ጉዞውን ያጠናቀቀ ሲሆን፥ በቀን ውስጥ ሳያቋርጥ ለ16 ሰዓታት ነበር ብስክሌቱን ሲያሽከረክር የነበረው።

ጉዞው በጣም አድካሚ እና አስቸጋሪ መሆኑን የተናገረው ማርክ፥ በጉዞው የመውደቅ አገዳ እንዳጋጠመው እና በዚህም በጥርሶቹ እና በክንዱ ላይ ጉዳት እንደደረሰበትም አስታውቋል።

ማርክ ቤማውንት ከዚህ ቀደም በብስክሌቱ ዓለምን የዞረ ሲሆን፥ በአሁኑ ጉዞው የዓለም ክብረወነስንን በእጁ ለማስገባት ያደረገው ሙከራም ተሳክቶለታል ነው የተባለው።

በብስክሌት ዓለምን በመዞር ተይዞ የነበረው ክብረ ወሰን 123 ቀናት ሲሆን፥ በኒውዚላንዳዊው አንድሮው ኒኮልሰን እጅ ነው የነበረው።

ማርክ ይህንን በብስክሌት ዓለምን የመዞር ጉዞ በ79 ቀናት በመጨረስ ክብረ ወሰኑን በእጁ አስገብቷል ነው የተባለው።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement