NEWS: በመዲናዋ 7 ሺህ 800 ኮድ ሶስት ሚኒባሶች ታፔላ ለጥፈው ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ ገብተዋል

                                           

በታሪክ አዱኛ

 በአዲስ አበባ ከተማ ከነሃሴ 17 ጀምሮ የተጀመረው የኮድ ሶስት ሚኒባስ የታፔላ የመለጠፍ ስራ ተጠናቀቀ ።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን በሁሉም ቅርጫፎች እንዲሰራጭ ባደረገው የመስመር ታፔላ 7 ሺህ 800 ኮድ ሶስት ሚኒባሶች ታፔላ ለጥፈው ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ ገብተዋል ነው ያለው ባለስልጣኑ ።

የባለስልጣኑ የትራንስፖርት ስምሪትና አከባቢ ጉዳዮች ቁጥጥር ዳሪክተር አቶ ጆኒ ተረፈ ለፋናብሮድካስቲግ ኮፖሬት እንደተናገሩት፥ በመዲናዋ የሚስተዋለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ የተጀመረው የኮድ ሶስት ሚኒባሶች ታፔላ የመለጠፍ ስራ ተጠናቆ ወደ መስመራቸው እንዲገቡ ተደርጓል።

ባለስልጣኑ ከ6 ሺህ በላይ ኮድ ሶስት ሚኒባሶች ላይ ታፔላ ለማሰራጨት ያቀደ ቢሆንም ከታቀደው በላይ ሊሰራጭ ችሏል።

ከትናንትናው እለት ጀምሮ የዲሲፒሊን አፈጻጸም መመሪያ መሰረትም ታፔላቸውን የማይለጥፉና ከመስመር ውጪ የሚሰሩ ሚኒባሶች ላይ ቅጣት መጀመሩንም ነው የተናገሩት።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement