NEWS: ተመድ በማይናማር የሮሂንግያ ሙስሊሞች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ዘመቻ አወገዘ

                                           

ተባበሩት መንግስታት ድርጅት በማይናማር የሮሂንግያ ሙስሊሞች ላይ የዘር ማጥፋት ዘመቻ እየተፈፀመ ነው ሲል አወገዘ።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ሃላፊ ዜይድ ራድ አልሁሴን፥ የማይናማር መንግስት የሀገሪቱ ወታደሮች በሮሂንግያ ሙስሊሞች ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ በአፋጣኝ እንዲያቆም አሳስበዋል።

የማይናማር ወታደሮች እየፈፀሙት ያለውን ጥቃት ተከትሎ እስካሁን ከ300 ሺህ በላይ የሮሂንግያ ሙስሊሞች ከመኖሪያቸው በመሸሽ ወደ ባንግላዴሽ ተሰደዋል።

የማይናማር ጦር፥ “የሮሄንግያ ታጣቂዎች ላደረሰቡኝ ጥቃት የአፀፋ ምላሽ እየሰጠሁ ነው፤ ጥቃቱ ንጹህ ዜጎችን አይመለከትም” ሲል አስተባብሏል።

ከሁለት ሳምንት በፊት የሮሂንግያ ታጣቂ ሰርጎ ገቦች በሀገሪቱ በሚገኙ 30 ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ ነው የማይናማር ወታደር አየጸፋ እርምጃ መውሰድ የጀመረው።

ከማይናማር ተሰደው የወጡ የሮሂንግያ ሙስሊሞችም፥ የማይናማር ጦር የሮሂንግያ ሙስሊሞች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ በሚል አሰቃቂ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን ይናገራሉ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ሃላፊ ዜይድ ራድ አልሁሴን፥ በአሁኑ ጊዜ በማይናማር ራክሂኔ እየተካሄደ ያለው ዘመቻ ተገቢ ያልሆነ ነው ብለዋል። 

በአካባቢው ያለውን ሁኔተ ሙሉ በሙሉ መመልከት አልተቻለም ያሉት ሃላፊው፥ ምክንያቱ ደግሞ የማይናማር መንግስት የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን መርማሪዎች እንዳይገቡ በመከልከሉ ነው ብለዋል።

ሆኖም ግን የመንግስታቱ ድርጅት ከስፍራው የተለያዩ ሪፖርቶች እና የሳተላይት ምስሎች እየደረሱት እንዶሀነ ያስታወቁ ሲሆን፥ ይህም የሀገሪቱ የፀጥታ ሀይሎች እና የሚሊሻ ታጣቂዎች የሮሂንግያ ሙስሊሞችን መንደር እያቃጠሉ እና እያባረሩ መሆኑን ያሳያል ብለዋል።

ከሁለት ሳምንት በፊት የሮሂንግያ ታጣቂ ሰርጎ ገቦች በሀገሪቱ በሚገኙ 30 ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸው ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም ፖሊስ ሰርጎ ገቦች ይገኙበታል በተባለውና አብዛኛዎቹ የሮሂንግያ ሙስሊሞች በሚኖሩበት ራክሂን በተባለ አካባቢ የአጸፋ እርምጃ በመውሰድ ላይ ይገኛል።

3በ0 ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ራሱን የሮሂንግያ ሙስሊሞች ነጻ አውጭ ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ሃላፊነቱን እንደሚወስድ አስታውቋል።

ቡድኑ በማይናማር አነስተኛ ቁጥር ያላቸው እነዚህ ሙስሊሞች ከፍተኛ ጭቆናና በደል እየተፈጸመባቸው ነው በሚል የማይናማርን መንግስት ይወቅሳል።

ይህን ለማስቀረትም የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አጠናክሬ እቀጥላለሁ ነው ያለው።

ቡድኑ በማይናማር መንግስት የሚቀርብበትን፥ የአሸባሪነት ውንጀላም ያጣጥላል።

የቡድኑ ታጣቂዎች በሮሂንግያ ሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለውን ጭቆናና በደል ለመቀልበስ የሚታገሉ መሆናቸውንም ነው ቡድኑ ነየሚገልጸው።

ባለፈው ዓርብ ከተከሰተው ግጭት ጋር ተያይዞም አብዛኛዎቹ ሰርጎ ገቦች የሆኑ ከ100 በላይ ሰዎች መሞታቸው ይነገራል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement