NEWS: ኒሳን ረዥም ርቀት ተጓዥ በኤሌክትሪክ ሀይል የሚንቀሳቀስ ተሽከርካሪ አስተዋወቀ

                                        

ኒሳን በኤሌክትሪክ ሃይለ የሚሰራ ረዥም ርቀት ተጓዥ አዲስ የተሽከርካሪ ሞዴልን አስተዋወቀ።

አዲሱ ሊፍ ኒሳን መኪና አንድ ጊዜ በተሞላ የኤሌክትሪክ ሃይል 240 ኪሎ ሜትር ያህል ይጓዛል።

አዲሱ ሞዴል ለአሽከርካሪዎች ምቹ ሲሆን፥ ባለፉት ሞዴሎች የነበሩ እያንዳንዱን ግብዓት ወስዶ በእሱ ላይ በማሻሻልና አዲስ መለያዎችን በመጨመር የተዘጋጀ መሆኑን ድርጅቱ አስታውቀዋል።

ማሻሻያዎቹ የተሽከርካሪ ማቆሚያ እና በነጠላ ፔዳል ማሽከርከርን ያካትታሉ።

ይህ ሞዴል አዳዲስ ፈጠራ እና ንድፎች የተካተቱበት መሆኑ ተነግሯል።

የፔዳል መቆጣጠሪያው በመጀመር፣ በማፍጠን፣ በማንሸራተትና በማቆም ላይ ያለውን ሂደት አውቶማቲክ ማቆሚያ ስርዓቱን ጠብቀው እንዲቆሙ እና አሽከርካሪዎች ወደ አደገኛ ቦታዎች እንዳያመሩ ያግዛል። 

ከዚህ ባሻገር አዲሱ ሞዴል፥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የካርቦን መጠን እንዲቀንስ ያግዛል ተብሏል።

ከጥቅምት ወር ጀምሮ በጃፓን ገበያ ላይ የሚውለው ባለ 40 ኪሎዋት ባትሪ አዲሱ ሊፍ በሚቀጥለው የፈረንጆቹ ዓመትም በገበያው ሰፊ ድርሻ የሚኖረው ይሆናል።

መነሻ መሸጫ ዋጋው 28 ሺህ 949 ነጥብ 55 የአሜሪካ ዶላር ነው ተብሏል።

አንዳንድ ባለሙያዎች እንደሚሉት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቴክኖሎጂ በፍጥነት እያደገ ነው።

ሆኖም ኒሳን ከጀነራል ሞተርስ እና ተስላ ጠንካራ ፉክክር እንደሚገጥመው ነው የተነገረው።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement