NEWS: የኢራኑ ፕሬዚዳንት ሳዑዲ አረቢያ ሽብርተኝነትም መደገፍ ማቆም አለባት አሉ

                                       

የኢራኑ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሮሃኒ ሳኡዲ አረቢያ ሽብርተኝነትን መደገፍ ማቆም አለባት ብለዋል።

እንደ የኢራን የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘገባ፥ ፕሬዚዳንቱ ሳኡዲ አረቢያን በየመን ውስጥ የሚንቀሳቀሱ አሸባሪዎችን ትደግፋለች ሲሉ ይከሷታል።

ሳኡዲ አረቢያ እና ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ላይ ተፅእኖ ፈጣሪ ሀገር ለመሆን በፉክክር ላይ የሚገኙ ሲሆን፥ ሁለቱም ሀገራት በየመን፣ በሶሪያ፣ በኢራቅ እና ሊባኖስ የሚንቀሳቀሱ የለያዩ የታጣቂ ቡድኖችን ይረዳሉ።

“ሳዑዱ አረቢያ በየመን የምታደርገው ጣልቃ ገብነት እና በየመን እና በሶሪያ የሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኖች የምታደርገው ድጋፍ በቴህራን እና በሪያክ መካከል ያለውን ግንኙነት እንዲሻክር አድርጓል” ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።

“ሳዑዲ አረቢያ ሽብረተኞችን ከመደገፍ መቆጠብ አለባት” ሲሉም ፕሬዚዳንት ሀሰን ሮሃኒ ተናግረዋል።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በመስከረም ወር 2014 ላይ በኢራን የሚደገፈው የሆውቲ ታጣቂዎች የየመን ዋና ከተማ ሰነዓን ተቆጣጥረው የነበረ ሲሆን፥ የሀገሪቱ ሁለተኛዋ ታላቅ ከተማ ኤደንን ለመቆጣጠርም እየተዋጉ እንደነበር ይታወሳል።

የሆውቲ ታጣቂዎች በተቆጣጠሩት ምላሽ ደግሞ በሳዑዲ አረቢያ የሚመራው አረብ ስቴት በሺአ ተዋጊዎች ላይ በከፈተው የጦር ዘመቻ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር በ2015 የየመንን መንግስት እንደገና መልሶታል።

በየመን ከተከሰተው የእርስ በእርስ ጦርነት ጋር በተያያዘ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር ከየካቲት ወር 2014 ወዲህ ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

ከ3 ሚሊየን በላይ ሰዎች ደግሞ የመኖሪያ ቄያቸውን ለቀው ለመሰደድ መገደዳቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖረት ያመለክታል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement