NEWS: ኦስትሪያ በዓለም የመጀመሪያውን የቢራ መዋኛ ገንዳ ይፋ አደረገች

                                            

ስክሎስ ስታርከንበርገር የተባለው ቢራ አምራች ድርጀት በዓለም የመጀመሪያውን የቢራ መዋኛ ገንዳ በኦስትሪያ ከፍቷል።

ድርጀቱ በሚያመርታቸው ቢራዎች የተሞሉ ሰባት የመዋኛ ገንዳዎችን ለደንበኞቹ ዝግጁ አድርጓል።

በእነዚህ በቢራ የተመሉ ገንዳዎች በአማካይ ለሁለት ሰዓት ያህል ለመዋኘትም 200 ፓውንድ ገንዝብ ወጪ ማድረግን ይጠይቃል ነው የተባለው።

በቢራ ገንዳ ውስጥ እየዋኙ ሰውነታቸውን ማዝናናትና የተጨናነቀውን አዕምሮ ማረጋጋት ለሚፈልጉ ሰዎች አጋጣሚው ጥሩ መሆኑ ተነግሯል።

እያንዳንዱ የመዋኛ ገንዳ 19 ሺህ 873 ሊትር ሙቅ ቢራና ትንሽ ውሃ ተጨምሮበት ነው ለዋና ዝግጁ የሚሆነው።

በዚህም መሰረት ማንኛውም ተጠቃሚ በገንዳው ውስጥ ተቀምጦ ገላውን መታጠብ አልያም መዋኘት ይችላል ተብሏል።

ቢራው በቫይታሚንና በካልሲየም የበለፀገ በመሆኑ ለቆዳ ጤንነት መልካም መሆኑ ተጠቅሷል።

ድርጀቱ የ700 ዓመት እድሜ ያለው ሴላር ካስል ቢራ ገበያው ስለተቀዛቀዘበት ነው የቢራ መዋኛ ገንዳ ከፍቶ የገላ መታጠቢያ አገልግሎቱን መስጠት የጀመረው።

በገንዳው ውስጥ ያለው ቢራ ሙቅ ሆኖ የሚቆይ ቢሆንም ቀዝቃዛ ቢራ የሚፈልጉ ዋናተኞች ካሉም ይቀርብላቸዋል።

ሆኖም በገንዳው ውስጥ ሆኖ ቢራ መጠጣት እንደማይመከር ድርጅቱ አስታውቋል።

ሰዎች በገንዳው ውስጥ ዋኝተውና ገላቸውን ታጥበው ሲጭርሱም፥ ቢራ መጠጣት ከፈለጉ ድርጀቱ ከሚያመርታቸው 13 የቢራ ዓይነቶች መርጠው ማዘዝ ይችላሉ።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement