NEWS: ብቸኛዋ ዝንጀሮ የዶሮ ጫጩቷን በማሳደግ ወዳጅ አድርጋታለች

                                       

በእስራኤል ራማት ጋን ሳፋሪ የእንስሳት ማቆያ ውስጥ የምትገኘው ዝንጀሮ ያልተመለደ ጓደኝነት መስርታለች።

በማቆያው ወስጥ ብቸኝነቷን ያልወደደችው ኒቭ የተሰኘችው ዝንጀሮ ባልተለመደ መልኩ ከዶሮ ጫጩት ጋር ነው ወዳጅነት የመሰረተችው።

የአራት አመቷ ዝንጀሮ የዶሮ ጫጩቷን እስከምታገኝ ድረስ ብቸኛና ጓደኛ አልባ ነበረች፤ ከሰሞኑም ከጫጩቷ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ትጀምራለች።

ዝንጀሮዋ ጫጩቷን አቅፋ የተመለከቱት የእንስሳት ማቆያው ተንከባካቢዎችም ጫጩቷን ከዝንጀሮዋ ማደሪያ በማስወጣት ራቅ ወዳለ ቦታ አባረዋታል።

ይሁን እንጅ ከሁለት ቀናት በኋላ ወደ ማቆያው በመመለስ ወደ ዝንጀሮዋ ማደሪያ ፍርግርግ አጥር ውስጥ በድጋሚ ገብታለች።

አሁን ላይም ትንሿ የዶሮ ጫጩት የኒቭ የቅርብ ወዳጅና ጓደኛ ስትሆን ከጠዋት እስከማታ አብረው ይውላሉ።

ለወትሮው ቢሆኖ ኖሮ እነዚህ ዶሮዎች የዝንጀሮዎች ምግብ ነበሩ፤ አሁን ግን የጠበቀ ወዳጅነት መሰርተዋል።

ስም አልባዋ ትንሿ ዶሮም በእንስሳት ማቆያው ውስጥ ፍርሃት ሲሰማትና ስትደነግጥ በኒቭ እቅፍ ውስጥ ትገባለች ነው የተባለው።

ከመሰሎቿ ተለይታ ጓደኛ አልባ የሆነችው ኒቭም የዶሮ ጫጩቷን በመንከባከብ መልካም ወዳጅነትን መስርታለች።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement