NEWS: ሰሜን ኮሪያ ሚሳኤል አስወነጨፈች

                                                

ሰሜን ኮሪያ ሰሜናዊ ጃፓንን ያቋረጠ ሚሳኤልን አስወነጨፈች።

ፒዮንግያንግ ሚሳኤሉን ያስወነጨፈችው ዛሬ ማለዳ ላይ ሲሆን፥ ሆካይዶ የተባለችን የጃፓን ደሴት ካቋረጠ በኋላ በባህር ላይ ወድቋል።

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ድርጊቱ አገራቸው ላይ አይታው የማታውቀውን ስጋት የደቀነ ነው ብለዋል።

በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ፒዮንግያንግ ተደጋጋሚ የሚሳኤል ሙከራዎችን ያደረገች ሲሆን፥ የባለስቲክ ሚሳኤል ነው ተብሎ የታመነው የዛሬው ጃፓንን ማቋረጡ ግን ያልተለመደ ነው።

ከዚህ ቀደም ሰሜን ኮሪያ በአውሮፓውያኑ 1998 እና 2009 ላይ ጃፓንን ያቋረጡ ሚሳኤሎችን ያስወነጨፈች ሲሆን፥ በወቅቱ የተወነጨፉት ሳታላይትን የተሸከሙ እንጂ የጦር መሳሪያዎች አይደሉም ስትል ነበር።

የዛሬውን የፒዮንያንግ ድርጊት ተከትሎ የፀጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባውን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement