ተፈጥሯዊ የእርግዝና መቆጣጠሪያ

                                                   

• የወር አበባ መፍሰስ ከጀመረበት ቀን አንስቶ እስከ አምስተኛው ቀን ድረስ መደበኛ የወር አበባ ጊዜ ነው፡፡ ይሄንን ጊዜ ጨምሮ የወር አበባው ከጀመረበት ቀን እስከ 8ኛው ቀን ድረስ (የመጀመሪያዎቹ ሰባት ቀናት) በአንፃራዊነት እርግዝና አይፈጠርም፡፡ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በዚህ ወቅት ያለመፈጠር እድሉ ከ95-100% እንደሆነ ይደርሳል፡፡
• ከ8ኛው ቀን እስከ 11ኛው ቀን ባሉት ሶስት ተከታታይ ቀናት ደግሞ በአንፃራዊነት እርግዝና ሊፈጠር ይችላል፡፡ ጥናቶቹ የሚጠቁሙትም እርግዝና የመፈጠሩ እድል ከ40-60% ይደርሳል፡፡
• ከ11ኛው ቀን ጀምሮ እስከ 17ኛው ቀን ድረስ ባሉት ተከታታይ 6 ቀናት እርግዝና የመፈጠር እድሉ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው፤ ከ80% በላይ፡፡
• ከ17ኛው ቀን አንስቶ እስከ 20ኛው ቀን ድረስ ባሉት 3 ተከታታይ ቀናት ደግሞ በአንፃራዊነት እርግዝና ሊፈጠር ይችላል፡፡ ጥናቶቹ የሚጠቁሙትም እርግዝና የመፈጠሩ እድሉ ከ40-60% እንደሆነ ነው፡፡
• ከ20ኛው ቀን አንስቶ የወር አበባ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ እርግዝና አይፈጠርም፡፡ በዚህ ወቅት እርግዝና ያለመፈተሩ እድል ከ95-100% ይደርሳል፡፡
• የሴቷ እንቁላል በወር አበባው ኡደት እኩሌታ ቀን ላይ (28 ከሆነ 14ኛው ቀን ላይ) ዝግጁ የሚሆን ሲሆን ከ12-24 ሰዓታት ለሚሆን ጊዜ ለፅንስ ዝግጁ እንደሆነ ሊጠብቅ ይችላል፡፡ በአንፃሩ የወንዱ የዘር ፍሬ ከወሲብ በኋላ በሴቷ ማህፀን ውስጥ ከ3 እስከ 5 ቀናት ሊቆይ የሚችል ሲሆን በአንድ ላይ ሲደመር ከአምስት ቀን እስከ ሰባት ቀናት ለሚሆን ጊዜ የእርግዝናው እድልን እጅግ ከፍተኛ ይሆናል ማለት ነው፡፡

ምንጭ:- ጤናችን

Advertisement