NEWS: የጃፓኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደርጋሉ

                                   

የጃፓኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታሮ ኮኖ ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደርጋሉ።

ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፀው፥ ሚኒስትሮቹ የሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት በሚጠናከርበት ሁኔታና በተለያዩ የዓለም አቀፍ የደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ ይወያያሉ።

ታሮ ኮኖ ጃፓን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የ100 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎም ይጠበቃል።

ኢትዮጵያና ጃፓን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከጀመሩ አንድ ምዕተ ዓመት ሊሞላቸው ነው።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

 

Advertisement