NEWS: በሱዳን የሩሲያ አምባሳደር በቤታቸው ሞተው ተገኙ

                                     

በሱዳን የሩሲያ አምባሳደር ካርቱም በሚገኘው መኖሪያቸው ሞተው መገኘታቸውን የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ አምባሳደር ሚርጋያስ ሺሪንስኪ በመኖሪያ ቤታቸው ሞተው መገኘታቸውን ጠቅሶ ለሩሲያ መንግስትና ህዝብ ሀዘኑን መግለጹን ሱና የዜና አገልግሎት በዘገባው ጠቅሷል።

የአምባሳደር ሺሪንስኪን ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ያደነቀው ሚኒስቴሩ ስለ አሟሟታቸው በዝርዝር የጠቀሰው መረጃ የለም።

ከፈረንጆቹ 1977 ጀምሮ በሩሲያ የዲፕሎማሲ ስራዎች ውስጥ ሲያገለገሉ የነበሩት ሺሪንስኪ በየመን፣ በሳዑዲ ዓረቢያ እና በሩዋንዳ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል።

ከ2013 ጀምሮ ደግሞ በሱዳን የሩሲያ አምባሳደር ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement