NEWS: ደቡባዊ ቻይናን የመታው ከባድ አውሎ ንፋስ 12 ሰዎችን ለህልፈት ዳርጓል

                                                  

ደቡባዊ ቻይናን የመታው ከባድ አውሎ ንፋስ 12 ሰዎችን ለህልፈት መዳረጉ ተነግሯል፡፡

“ሃቶ” የሚል መጠሪያ የተሰጠው አውሎ ንፋሱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱ ተነግሯል።

በሰዓት 175 ኪሎ ሜትር የሚምዘገዘገው አውሎ ንፋሱ ከባድ ጎርፍ እንዳስከተለ ነው የተገለጸው፡፡

የኤሌክትሪክ ሀይል ማስተላለፊያ መስመሮች እንዲቋረጡ፣ የተለያዩ ንብረቶች እንዲወድሙ እና የመሬት መንሸራተት እንዲከርስ አድርጓል።

በጉዋንዶንግ ግዛት ዡዋይ ከተማ አቅራቢያ መነሻውን ያደረገው “ሃቶ” አውሎንፋስ በሆንግ ኮንግም ከፍተኛ ስጋት በመደቀኑ ነዋሪዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያድርጉ ማስጠንቀቂያ ተላልፏል።

ሽንዋ በድረገፁ ባወጣው መረጃ አውሎ ንፋሱ በዋናነት በተከሰተበት አካባቢ ከ27 ሺህ በላይ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው እንዲነሱ ተደርጓል።

በትናንትናው እለትም በሆንግ ኮንግ የንግድ ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች፣ የባቡር ጣቢያዎች እና አውሮፕላን ማረፊያዎች ተዘግተው ውለዋል።

አውሎ ንፋሱ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ማዕከል የሆነችውን ሆንግ ኮንግ ወደ 1 ቢሊየን ዶላር ያሳጣል ተብሎ እንደሚገመትም ተጠቅሷል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

 

Advertisement