NEWS: አሜሪካ ከ241 ዓመት በኋላ የመጀመሪያዋ የሆነውን ሙሉ የፀሃይ ግርዶሽን ዛሬ ታያለች

                                           

ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ የሚያቋርጥ የፀሐይ ግርዶሽ ይኖራል።

ታሪካዊ ክስተቱ “ታላቁ የአሜሪካ የፀሃይ ግርዶሸ” ለመባል በቅቷል።

በአጠቃላይ በ14 የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች ጨረቃ ፀሃይን ሙሉ በሙሉ ስትጋርድ የማየት እድሉ አላቸው።

የግርዶሽ ሙሉው መንገድ ኦሬጎን፣ አይዳሆ፣ ዋዮሚንግ፣ ነብራስካ፣ ሚስዩሪ፣ ኬንታኪ፣ ቴነሲ፣ ጆርጂያ፣ ሰሜን ካሮላይና እና ደቡብ ካሮሊና ግዛቶች ስለሚያዳርስ በነዛ ግዛቶች የሚኖሩ ዝጎች ይህንን ሁኔታ የማየት ዕድል ያገኛሉ፡፡.

በዚህም መሰረት ግርዶሹ በተወሰኑ አካባቢዎች ሙሉ ግርዶሽ ሲሆን፥ ከፊል ግርዶሽ ሥር የሚያርፉ ስፋት ያላቸው የዩናይትድ ስቴትስና የካናዳ አካባቢዎች አሉ።

ዋሺንግተን ዲሲና አካባቢዋ ከፊል ግርዶሽ ሥር ከሚያርፉት ናቸው።

ምንም እንኳን በብዙ ቦታዎች ግርዶሹ ሙሉነት ቢኖረውም በየአከባቢው ያሉ ሰዎች ግርዶሹን ለማየት የሚኖራቸው ዕድል ከሁለት ደቂቃ እስከ 40 ሴኮንድ በመሆኑ ቆይታው አጭር ይሆናል።

ያለፈው የፀሐይ ግርዶሽ ዩናይትድ ስቴትስ ምድር ላይ የታየው ከዛሬ 38 ዓመት በፊት ሲሆን፥ እንዳሁኑ ፀሃይ በጨረቃ ሙሉ በሙሉ የተጋረደችበትን አጋጣሚ ያየችው ግን ከ241 በፊት ነው። 

እንዲህ ዓይነት ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ ያቋረጣት ግርዶሽ የነበረው ግን የዛሬ መቶ ዓመት ነበር።

ጨረቃ ወደ ፀሐይ አንፃር ገብታ ሙሉ በሙሉ እስክትወጣ ሙሉው የግርዶሽ ጊዜ 2 ሰዓት ከ44 ደቂቃ ነው የሚሆነው።

በተለይ ለዋሺንግተን ዲሲና አካባቢዋ ነዋሪዎች እጅግ የተመቸ እንደሚሆን ተተንብይዋል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ (FBC)

Advertisement