NEWS: በምዕራብ አርሲ 108 ልጆችና የልጅ ልጆች ያፈሩት የ107 ዓመት አዛውንት የ33 ዓመቷን ሴት አግብተዋል

                                        

በብዛት የተለመደው እንድ ሰው በወጣትነት የአድሜ ክልል ወስጥ ሲገባ ትዳር ይመሰርታል።

አልፎ አልፎ ግን በስራ ምክንያትም ይሁን በሌሎች የኑሮ ምክንያቶች አንዳንዶች እድሜያቸው ገፋ ካለ በኋላ በስተርጅና ትዳር ሲመሰትሩም ያጋጥማል።

በምዕራብ አርሲ ዞን ሻሸመኔ ወረዳ ግን የተከሰተው ከዚህም ለየት የሚል ሲሆን፥ የ107 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ የሆኑት አዛውንት ባሳለፍነው እሁድ ድል ባለ ሰርግ ማግባታቸው ነው የተሰማው።

ሙሽራው አዛውንት ሃጂ አብዱልቃድር ዴከማ ዲዶ ይባላሉ፤ የሻሸመኔ ወረዳ የዳኒሳ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ፥ በ1902 ዓ.ም እንደተወለዱም ይናገራሉ።

የተለያዩ ሀይማኖታዊ ትምህርት ላይ ከቆዩ በኋላ የመጀመሪያ ባለቤታቸውን በ1942 ዓ.ም ማግባታቸውን የሚናገሩ ሲሆን፥ ከመጀመሪያ ባለቤታቸው ጋርም ዘጠኝ ልጆችን አፍርተዋል።

ሀጂ አብዱልቃድር ሁተኛ ባለቤታቸውንም በ1956 አግበት አርበው መኖር እንደጀመሩም ይናገራሉ።

ከሁለቱ የትዳር አጋሮቻቸው በርካታ ልጆችን መውለዳቸውን የሚናገሩት ሀጂ አብዲልቃድር፥ በአሁኑ ጊዜ 9 ሴት እና 10 ወንድ ልጆቻቸው በህይወት እንዳሉም ተናግረዋል። 

በአሁኑ ጊዜም የበኩር ልጃቸው የ60 ዓመት አዛውንት ነው።

ሀጂ አብዱልቃድር ልጆቻቸውን እና የልጅ ልጆቻቸውን ጨምሮ እስካሁን 108 የቤተሰብ አባላት አፍርተዋል።

ታዲያ ሁለተኛዋ ባለቤታቸውን በሞት ያጡት ሀጂ አብዱልቃድር የመጀመሪያ ባለቤታቸውም ድካም ስለተጫጫናቸው የሚንከባከበኝ አጣሁ ይላሉ።

የሚንከባከባቸው ከማጣት እና አዲስ ሚስት ለማግባት ካላቸው ፍላጎት የተነሳም ሶስተኛ ሚስት ማግባት እንዳላቸው ከውሳኔ የደረሱት ሀጂ አብዱልቃድር፥ ይህንን ሀሳባቸውንም ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመወያየት ተቀባይነት ያገኝላቸዋል።

በአካባቢው የጋብቻ ባህል መሰረትም ለጋብቻ የፈለጓት ሴት ቤተስብ ጋር ሽማግሌ ልከው ያስጠየቁ ሲሆን፥ ጥያቄያቸውም እሺ የሚል መልስ ያገኛል።

በዚህም መሰረት የ107 ዓመቱ አዛውንት ሀጂ አብዱልቃድር ባሳለፍነው እሁድ ነሃሴ 7 2009 ፉሮ ጉዬ የተባለች የ33 ዓመት ሴት ዘመድ አዝማድ በተገኘበት ድል ባለ ሰርግ ማግባታቸው ተነግሯል።

“በዚህ እድሜዬ በሰርግ ማግባቴ በጣም አስደስቶኛል” የሚሉት ሀጂ አብዱልቃድር፥ 3ኛ ባለቤታቸውን በልዩ አይን እንደሚያይዋት እና “የእድሜ ልዩነት እንዳለው ሰው ሳይሆን እንደማንኛወም ሰው አብራኝ እድትኖር እፈልጋለው” ብለዋል።

ፈጣሪ ከፈቀደም ከሶስተኛ ባለቤታቸው ጋር ልጆች የመውለድ ሀሳብ እንዳላቸውም ሀጂ አብዱልቃድር ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በፍቅር እና በደስታ አብረዋት መኖር እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል።

ምንጭ:- የሸገር FM 102.1 ሬዲዮ

 

Advertisement