የዛሬ የዕለተ አርብ ነሐሴ 5 ቀን 2009 የሸገር ወሬዎች::

                              

የመንግሥት ባለ በጀት መሥሪያ ቤቶች ወጪያቸውን በአግባቡና ሕግን ተከትለው እንዲጠቀሙ ጥብቅ መመሪያ ተሰጣቸው፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)

በለገዳዲ ጥልቅ የውሃ አገልግሎት ማቆም፤ ከ100 ሺ በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ለውሃ እጦት ተጋልጠዋል ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)

ኢትዮጵያን በተመለከተ አሜሪካ ያወጣችውን የጉዞ ማስጠንቀቂያ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃወመው፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ተጠያቂነትን ለማጠናከር ለሚከወነው ሥራ መንግሥትና የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የሚያደርጉትን ድጋፍ ሊያበረቱ ይገባል አለ፡፡ (እሸቴ አሰፋ)

ለህክምና ወደ አዲስ አበባ መጥተው የእለት ጉርስና መጠለያ አጥተው የሚቸገሩ የጥቁር አንበሣ ታካሚዎችን የሚደግፈው ጎጆ የህሙማን ማህበር ለህሙማኑ መጠለያ እንዲሆን ያስገነባው ህንፃ ተጠናቀቀ፡፡ ታካሚዎቹን በመጠለያ ለማሳረፍም ቀሪ ቁሶችን ለማሟላት የሚያስችል የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም አዘጋጅቻለሁ ብሏል፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)

በአዲስ አበባ መንገዶች ላይ በየእለቱ ቅሬታ የሚደመጥ ቢሆንም የኛ አካባቢ የንግድ ተቋማትን ተከራይ እስከ ማሳጣት የደረሰ፣ መግቢያ መውጫ ያሳጣ ነው ይላሉ የገርጂ ነዋሪዎች፡፡ (ምሥክር አወል)

የአፍሪካ የኩባንያ አስተዳደር አለም አቀፍ ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም)

የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ የሠራተኞቻቸውን የጡረታ መዋጮ በጊዜው ገቢ ያላደረጉ 12 ድርጅቶችን ንብረት አሳገድኩ አለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)

የሙሥና ወንጀሎችን ለመከላከልና ለማጋለጥ የህግ አስከባሪ ተቋማት የሚሰሩበት እቅድ ተዘጋጅቷል ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም)

ምንጭ:- የሸገር FM 102.1 ሬዲዮ

Advertisement