የዛሬ የዕለተ ማክሰኞ ነሐሴ 2 ቀን 2009 የሸገር ወሬዎች

                                       

በኢትዮጵያ የእርዳታ ፈላጊ ዜጎች ቁጥር ጨምሯል ተባለ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)

የእንባ ጠባቂ ተቋም ሠራተኛ የነበረው አቶ በላቸው ደባሎ ጉቦ በመቀበል ወንጀል ተጠርጥሮ ትላንት ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡ (እሸቴ አሰፋ)

በኢትዮጵያ የሚደርሰው የትራፊክ አደጋ ከመቀነስ ይልቅ እየጨመረ በመሄዱ በዚህ አመት የተጀመረው ሀገር አቀፍ የትራፊክ አደጋ ዘመቻ በሚቀጥለው አመትም ይቀጥላል ተባለ፡፡ ዘንድሮም ከ4 ሺ ሰዎች በላይ በትራፊክ አደጋ ሞተዋል፡፡ (ምህረት ስዩም)

ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር የበቆሎ ማሳ 600 ሺ ሄክታሩን የወረረውን የአሜሪካ መጤ ተምች 75 በመቶ ማጥፋት ተችሏል ሲል የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ (ምሥክር አወል)

የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ዘንድሮ በጥናት ካገኛቸው 76 ያህል ምርጥ ዘሮች ለገበሬው መለቀቅ የቻሉት 48 ያህሉ ናቸው ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)

አብዛኛዎቹ በአዲስ አበባ የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች የሥራ ፍቃዳቸውን በጊዜው የማያሣድሱ ናቸው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በዚህ ዓመት ከ65 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቁ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ውል ማሰሩን ተናገረ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ከደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዬች መሀከል የቀን ገቢ ግምቱን በተመለከተ 60 በመቶዎቹ ላይ ውሣኔው ፀንቷል አለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)

በ2009 ዓ.ም ከ498 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ከሀገር ሀገር አጓጉዣለሁ ሲል የፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ተናገረ፡፡ (ምህረት ስዩም)

የሦስት የመንግሥት ፋይናንስ ድርጅቶች ጠቅላላ ሀብት ከ523 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱ ተሠማ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)

ምንጭ:- የሸገር FM 102.1 ሬዲዮ

Advertisement