የዛሬ የዕለተ አርብ ሐምሌ 28 ቀን 2009 የሸገር ወሬዎቻችን፣

                            

በሚቀጥሉት 10 ቀናት ከባድ ዝናብ ሊጥል ይችላልና ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም)

በአዲስ አበባ ከሚገኙ 46 ሺ በላይ ወላጆቻቸውን በሞት ካጡ ህፃናት ከግማሽ በላይ የሆኑት ወላጆቻቸውን ያጡት በኤች.አይቪ.ኤድስ ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)

የእሣትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ለሚደርሱብኝ ወቀሳ እኔ ብቻ ተጠያቂ አይደለሁም ሌሎች መስራት በነበረባቸው ሥራዎች እየተወቀስኩ ነው አለ፡፡ (ምሥክር አወል)

የአሰሪውና የሠራተኛው ግንኙነት ሰላማዊ መሆን ለኢንዱስትሪው ሰላም ወሳኝ በመሆኑ አሰሪዎች ሠራተኞቻችሁ እንዲደራጁ ፍቀዱላቸው፤ ጥቅሙ የጋራ ነው ተብላችኋል፡፡ (አስፋው ስለሺ)

የሰነድ መብዛት የፈረሱና ወደ ግል የተዛወሩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሠራተኞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ በተገቢው ፍጥነት እንዳይመለስ ያደረገ አንዱ ምክንያት ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)

ለ10 ወራት ተጥሎ የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተነሳ፡፡ ሦስት ሚኒስትሮችም ዛሬ ተሾመዋል፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)

የቀድሞው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ድኤታና የምክር ቤቱ አባል የሆኑት የአቶ አለማየሁ ጉቱ ያለመከሰስ መብት ተነሳ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉ የመንግሥት ኃላፊዎች ጉዳይ በፍርድ ቤት መታየቱ ቀጥሏል፡፡ (እሸቴ አሰፋ)

ምንጭ:- የሸገር FM 102.1 ሬዲዮ

Advertisement