NEWS: ፌስቡክ ትልቅ ስክሪን ያለው የቪዲዮ መልዕክት መለዋወጫ መሳሪያ እየሰራ ነው::

                                        

ፌስቡክ ሰዎች “በአካል ተገናኝተው እንደሚያወሩ ያህል እንዲሰማቸው የሚያደርግ” ትልቅ ስክሪን ያለው የቪዲዮ መልዕክት መለዋወጫ መሳሪያ እየሰራ መሆኑ ተገለፀ።

የቪዲዮ መልዕክት መለዋወጫ መሳሪያው 13 በ15 ኢንች የስክሪን ስፋት ያለው ሲሆን በቤት ውስጥ ጥቅም ላይ እንዲውል ታስቦ ነው እየተሰራ ያለው።

የላፕቶፕ መጠን ያለው መሳሪያው ተች ስክሪን እና የስማርት ካሜራ ቴክኖሎጂ ባለቤት ሲሆን፥ በቴክኖሎጂው የሚነጋገሩ ሰዎች አንድ ክፍል ውስጥ ሆነው የሚያወሩ እንዲመስላቸው ያደርጋል ተብሏል።

ይህ መሳሪያ ፌስቡክ ባለፈው አመት የሀርድዌር ምርቶችን እንዲያቀርብ ያቋቋመው 8 ላብ ያመረተው የመጀመሪያ ምርት ነው።

ለአዲሱ የፌስቡክ የቪዲዮ መልዕክት መለዋወጫ መሳሪያ ቅርበት ያላቸው ሰዎች በቀጣዩ አመት ለገበያ እንደሚውል ለብሉምበርግ ተናግረዋል።

360 ዲግሪ የሚዞር ካሜራ የተገተመለት መሳሪያው አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም እንደሚጠቀምም ነው የገለጹት።

ፌስቡክ ከጎግል ሆም እና አማዞን ኤኮ ጋር ለመፎካከርም ስታንዳሎን የተሰኘ ስማርት ስፒከር እየሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የኩባንያው ሁለት አዳዲስ ስራዎች የፌስቡክ መስራች ማርክ ዙከርበርግ አለምን የማስተሳሰር አላማ አካል ናቸው ተብሏል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement