የዛሬ የዕለተ ማክሰኞ ሐምሌ 25 ቀን 2009 የሸገር ወሬዎቻችን፣

                                                     

የታዳጊዎች የኤች.አይቪ ኤድስ ተጋላጭነት ከፍተኛ እየሆነ ቢመጣም ወላጆች ልጆቻችሁን መቆጣጠሩ ላይ ግን እምብዛም ናቸው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ህሙማን የሚያስፈልገውን ኦክሲጂን በራሱ አምርቶ ለማቅረብ የማያስችለውን ግንባታ አጠናቆ ሥራ ለመጀመርም ፍተሻ እያደረገ ነው ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም)

በትላንትናው እለት መሳለሚያ እህል በረንዳ ተገኝተን እንደቃኘነው የ1 ኩንታል ማኛ ጤፍ ዋጋ ከ2 ሺ እስከ 2 ሺ 800 ብር ሲሸጥ ውሏል፡፡ (በየነ ወልዴ)

የኢትዮጵያ የውስጥ ደዌ የህክምና ማህበር ተከታታይ የምዘና ትምህርት በሥራ ላይ ላሉ ባለሞያዎች ለመስጠት የመንግሥትን ይሁንታ እየጠበኩ ነው አለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ 2ኛ ዓመታዊ ጉባዔውን እያካሄደ ነው፡፡ (ምሕረት ስዩም)

የአበባና አትክልት ፍራፍሬ አምራቾች በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚረዳቸውን ሰርተፍኬት የሚያገኙበት መላ እየተመከረ ነው፡፡ (ምህረት ስዩም)

ለአዲስ አበባ ተነሺዎች ከ750 ሚሊዮን ብር በላይ ካሳ ተከፍሏቸዋል፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)

የታላላቅ ሰዎች የመቃብር ሃውልቶች ሊታደሱ ነው፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ

ምንጭ:- የሸገር FM 102.1 ሬዲዮ

Advertisement