SPORT: ማንችስር ሲቲ ቤንጃሚን ሜንዲን ከሞናኮ ማስፈረሙ ተረጋገጠ::

                                    

ማንችስተር ሲቲ ፈረንሳያዊውን ቤንጃሚን ሜንዲን በአምስት ዓመታት የኮንትራት ስምምነት ማስፈረሙንና 22 ቁጥር መለያ ለብሶ እንደሚጫወት በድረገፁ በይፋ ገልፅዋል።

የ23 ዓመቱ የግራ መስመር ተከላካይ ሜንዲ በአሜሪካ የቅድመ ልምምድ የውድድር ዝግጅት ጉዞ ላይ የሚገኘውን የፔፕ ጋርዲዮላውን ቡድን እንደሚቀላቀልም ክለቡ ገልፅዋል።

ሲቲ ለተከላካዩ 52 ሚ.ፓ የዝውውር ክፍያ እንደከፈለ ከእንግሊዝ የወጡ ዘገባዎች ያመለከቱ ሲሆን፣ በዚህም መሰረት ሲቲ ለክረምቱ ዝውውር 200 ሚ.ፓ ወጪ በማድረግ በአንድ የዝውውር መስኮት ከፍተኛ ወጪ በማውጣት የዓለም ክብረወሰንን መስበር ችለዋል።

ባለፈው ክረምት የሊዮናርዶ ጃርዲሙን ክለብ ሞናኮን በአምስት ዓመት ስምምነት ተቀላቀሎ የነበረው ሜንዲ በፈረንሳዩ ክለብ ለአንድ ዓመት ቆይታ ካደረገ በኋላ “ማንችስተር ሲቲን በመቀላቀሌ ተደስቻለሁ።” ሲል ዜጎቹን በመቀላቀሉ የተሰማውን ስሜት ገልፃ “እነሱ ከአውሮፓ መሪ ክለቦች መካከል የሚመደቡ ናቸው። እንደፔፕ ጋርዲዮላ ያለ በማጥቃት ላይ ላመዘነ አጨዋወት ከፍተኛ መስዋዕትነት የሚከፍል አሰልጥኝ አላቸው።

“እርግጠኛ ነኝ በቀጣዮቹ ጥቂት ዓመታት ውስጥ ስኬታማ እንሆናልን።” ሲል ገልፅዋል።

ሜንዲ ሞናኮዎች በሁሉም ውድድሮች ላይ 159 ግቦችን ከመረብ ላይ በማስረፍ የሊግ 1 ክብርን ሲቀዳጁና በሻምፒዮንስ ሊጉ እንዲሁም በፈረንሳይ ዋንጫ እስከ ግማሽ ፍፃሜ ድረስ እንዲበቁ ያስቻላቸውን በማጥቃት ላይ የተመሰረተ አጨዋወት እንዲኖራቸው በግራ ክንፍ በኩል ቁልፍ ሚና ነበረው።

ምንጭ:- ኢትዮአዲስ ስፖርት

Advertisement