NEWS: የሶማሊያ መንግስት ለህዝባዊ አስተያየትና ምክር መቀበያ የሚያገለግል ድረ ገፅ ይፋ አደረገ

                                         

የሶማሊያ መንግስት ለህዝባዊ አስተያየትና ምክር መቀበያ የሚያገለግል ይፋዊ ድረ ገፅ አስተዋውቋል፡፡

ለህዝብ አስተታየት እና ምክር መቀበያ የሚገለገልገለው ድረ ገፅ የፋ የሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን ካይሬ ነው፡፡

የሀገሪቱ ዜጎች ጥያቄዎቻቸውን፣ አስተያየታቸውን እና ምክራቸውን በኢሜይል ለመንግስት ተቋማት እንዲያቀርቡ እና ተቋማቱም ህዝብን እንዲያዳምጡ ያግዛል ተብሏል፡፡

ይህን ተግባር የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በበላይነት የሚያስተዳድረው ሲሆን፥ መረጃዎቹን በማሰባሰብ በአስተዳደር እና በአገልግሎት አሰጣጥ ረገድ ያሉ ጉድለቶችን የመንግስት ተቋማት እንዲያሟሉ ያደርጋል ነው የተባለው፡፡

አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ወደ ስልጣን በመጡበት ወቅት የግልፅነት ፖሊሲን ተግባራዊ ለማድረግ ለከህዝቡ ጋር ተባብረው እንደሚሰሩ መናገራቸው ይታወቃል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ባሳለፍነው መጋቢት ወር ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ከጋዜጠኞች፣ ከሲሲቪክ ማህበራት እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ባደረጉት ውይይት ሶማሊያን ሰላማዊ እና የበለፀገች ለማድረግ ተባብረን መስራት ይገባናል ማለታቸው አይዘነጋም፡፡

“የተሰደዱ ወገኖቻችንን ለማስመለስ፣ ሀገራችንን የተረጋጋች ለማድረግ፣ መንገስት እና ህዝቡ በጋራ ለጋራ ስኬት መስራት አለባቸው” ብለዋል ፋርማጆ፡፡

በአዲሱ ድረገፅም ዜጎች በአረብኛ፣ በሶማሊኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች አስተያየቶችን መላክ ይችላሉ ተብሏል፡፡

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

 

 

Advertisement