የዛሬ የዕለተ አርብ ሐምሌ 14 ቀን 2009 የሸገር ወሬዎች::

                                        

የሳውዲ አረቢያ መንግሥት የሰጠው ተጨማሪ የአንድ ወር ጊዜ ሊጠናቀቅ የቀሩት ሦስት ቀናት ቢሆኑም ሀገር ቤት የደረሱት ኢትዮጵያውያን ቁጥር አነስተኛ ነው ተባለ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)

የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ከተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የማያገለግሉ ንብረቶችን በመሸጥ ያገኘው ገቢ ከአምናው በግማሽ ያነሰ ነው ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)

በተማሪዎች የትምህርት ቤት ምገባ የበጎ አድራጎት ተግባር ላይ የተሰማራው የእናት ወግ ማህበር ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ተሰጠው፡፡ (ምህረት ስዩም)

በኢትዮጵያ አሰሪዎች ፌዴሬሽንና በኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን የተዘጋጀው ሞዴል የህብረት ስምምነት ትላንት በኢሊሌ ሆቴል ቀጥታ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት እንዲወያዩበት ተደርጓል፡፡ (አስፋው ስለሺ)

የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ያለመ ምክክር ሊካሄድ ነው፡፡ (ምህረት ስዩም)

ዘንድሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ትኩረት የሚሹ ተብለው የተለዩ በሽታዎች መከላከያና መፈወሻ የሚውሉ ከ4 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው መድሃኒቶች ተሰራጭተዋል ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)

በአዳማ ከተማ ወላጅ እናቱን የገደለ ግለሰብ በእሥራት ተቀጣ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)

ምንጭ:- የሸገር FM 102.1 ሬዲዮ

Advertisement