ለልጅ ፖፖ ማስተማር::

                                                    

ልጆች ሽንትና ሰገራቸውን መቆጣጠር የሚጀምሩት ከ12-18 ባሉት ወራት ውስጥ ነው። ብዙ ህፃናት ፖፖ የሚጀምሩት ከአንድ እስከ ሶስት ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ ነው።

ፖፖ መጀመር ያለበትን ጊዜ ለማወቅ በልጁ እድገት ላይ ያሉ ብዙ ነገሮችን ማስተዋል ይጠይቃል። ለዚህም ህፃኑ የአእምሮ ዝግጅት ያስፈልገዋል። ይህ ደረጃ የሚደረስበት ጊዜም ከልጅ ልጅ ይለያያል። በዚህም ምክኒያት ፖፖ መጀመር ያለበትን ትክክለኛ ጊዜ ለማስቀመጥ ያስቸግራል።ለሽንትና ሰገራ የተለየ ቦታ እንዳለው ማገናዘብ፣ ከመቀመጥ በፊት ሱሪ ማውለቅ እንዳለበት ማወቅ የመጀመርያ እንቅስቃሴዎች ናቸው።

አልጋ ላይ መሽናት መቼ መቆም አለበት?
ይህ ትላልቅ ህፃናት ላይም በተለይ በእንቅልፍ ሰዓት ሊታይ የሚችል ስለሆነ አያስጨንቅም። ልጆች ሽንታቸውን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር እንዲችሉ ውስጥ የሚመረተው ተቆጣጣሪ ሆርሞን ተመርቶ ስራውን መጀመር አለበት። ይህ ደግሞ ብዙ ጊዜ ሊፈጅ ይችላል።አልጋ ላይ መሽናት አሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚደርሰው ልጁ እድሜው ከ5 ዓመት በላይ ሆኖ በሳምንት ቢያንስ ሁለት ጊዜ በየቀኑ አልጋ የሚያረጥብ ከሆነ እንዲሁም ልጁ ከእንቅልፉ ከነቃ በኋላም ሽንቱ የሚመጣ ከሆነ ነው፡፡

ምንጭ:- ዘ ዶክተርስ

Advertisement