የዛሬ የዕለተ ረቡዕ ሐምሌ 12 ቀን 2009 የሸገር ወሬዎች::

                                                                                   

የያንግ ሩት እንግሊሽ ስኩል ትምህርት ቤት ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ውጤት ጠፍቷል ምክንያቱ በህትመት ወቅት ባጋጠመው የኃይል መቆራረጥ ነው ሲል የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ተናግሯል፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)

የተለያዩ ጥፋት የተገኘባቸው ዘጠና ስምንት አቅራቢዎች በማንኛውም የመንግሥት የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ ታገዱ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)

በተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች አለመናበብ ምክንያት የመጀመሪያው የግል ባህል ማዕከል ሊፈርስ ነው ይላሉ የማዕከሉ ባለቤት፡፡ አፍራሹ አካል የተሻሻለው ማስተር ፕላን እንዲፈርስ ስላስገደደ ነው ይላል፡፡ (ምሥክር አወል)

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከ2 ሚሊዮን በላይ መፅሐፎችን አሳትሞ ለመጪው የትምህርት ዘመን አያከፋፈለ መሆኑን ተናገረ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)

የጨሞ ሃይቅ አሳዎችን ከህገ-ወጥ አስጋሪዎች ለመጠበቅ 24 ሰዓት ይሰራል ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)

አሥር ዓመታት ያለፈው የመሬት ይዞታ አዋጅ ፀደቀ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)

የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የከፋ የገንዘብ አጠቃቀም ችግር እንዳለባቸው የተናገሩ ተቋማትን የክትትል ትኩረቴ አደርጋለሁአለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)

እየፈረሱ ያሉ ሁለት የሀረር ታሪካዊ ቤቶች እድሣት ሊደረግላቸው ነው፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)

ምንጭ:- የሸገር FM 102.1 ሬዲዮ

 

Advertisement