ቡአ (ኸርኒያ)

                                                   

ኸርኒያ እንዴት ይከሰታል?
ኸርኒያ በጡንቻዎች መድከም እና መወጠር ምክንያት የውስጠኛው የሠውነት ክፍል ወደ ውጪ መውጣት የሚያስከትል በሽታ ነው፡፡
 ጡንቻዎች እንዲደክሙ አስተዋጽዎ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል፡-
• የእድሜ መግፋት
• የቆየ ሳል
• በአደጋ ወይም በቀዶ ጥገና ምክንያት ጡንቻዎች ሲጎዱ
• በተፈጥሮ የሆድ ክፍል ከማህጸን ጋር መግጠም አለመቻል
 ጡንቻዎች እንዲወጠሩ አስተዋጽዎ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል፡-
• እርግዝና
• የሆድ ድርቀት
• ከባድ እቃዎችን ማንሳት
• ለረጅም ጊዜ የቆየ ሳል እና ማስነጠስ

ለኸርኒያ የሚያጋልጡ ሁኔታዎች
• በዘር ውስጥ የዚህ በሽታ ተጠቂ መኖር
• ከልክ በላይ ያለፈ ውፍረት
• የቆየ ሳል
• የቆየ የሆድ ድርቀት
• ሲጃራ ማጨስ

የኸርኒያ ምልክቶች
• በተጎዳው ቦታ ላይ የሚታይ እብጠት
• የተጎዳው ቦታ ላይ ህመም ወይም ምቾት ማጣት በተለይ በማሳል ወይም እቃ በማንሳት ወቅት
• የድካም ስሜት
• በሆድ አካባቢ የመድከም እና የመወጠር ስሜት
• በደረት እና በሆድ አካባቢ የማቃጠል ስሜት
• የደረት ላይ ህመም
• ለመዋጥ መቸገር

ኸርኒያን እንዴት መከላከል ይቻላል
1.አለማጨስ
2.ሳል ካለ ቶሎ ወደ ህክምና መሄድ
3.የሠውነት ክብደትን መቆጣጠር
4.ከበድ ያሉ እቃዎችን አለማንሳት
5.የጉሎ ዘይትን መጠቀም

ምንጭ:- ጤናችን

Advertisement