ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቲውተር ገጻቸውን የሚከተሉ ሰዎችን ብሎክ በማድረግ ተከሰሱ

ክሱን የመሰረቱት ሰባት ተከታዮቻቸው ሲሆኑ ሃሳብን በነጻነት የመግለፅ መብታችንን ተጋፍተዋል በሚል ነው፡፡

ብሎክ የተደረጉት የቲውተር ደንበኞች ፕሬዝዳንቱ በገጻቸው የሚያስተላልፏቸውን መልዕክቶች የሚተቹና የሚቃወሙ ሃሳቦችን የሚሰነዝሩ  የነበሩ ናቸው ተብሏል፡፡

በዚህም የሃገሪቱን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን  ተጋፍተዋል ነው ያለው የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ፡፡

ከፕሬዝዳንቱ በተጨማሪ በነጩ ቤተ-መንግስት ጸሓፊ ሲን ሰፓይሰርና  የመሃበራዊ ድረ-ገጾች ዳሬክተር ዳኒኤል እስካቪኖ ስማቸው በክሱ መዝገብ ውስጥ ሰፍሯል ነው የተባለው፡፡

አሁን ለይ የፕሬዝዳንቱ የቲውተር ተከታዮች ከ 33 ሚሊዮን በላይ ሆኗል፡፡

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፉት 30 ዓመታት 4000 የሚሆኑ ክሶች እንደቀረበባቸው ተዘግቧል፡፡

ምንጭ-ቢቢሲ

 

Advertisement