በደቡብ ኮሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከፍተኛ ባለሥልጣን በመድፈር ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው

የኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተልኩ ነው ብሏል፡፡

ሚኒስቴሩ ባወጣው ሪፖርት ባለሥልጣኑ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ተቀጥራ የምትሰራ ሴትን የእራት ግብዣ ካደረጉላት በኃላ በሃይል አስገድደው ደፍሯዋታል ነው ያለው፡፡

የመድፈር ወንጀል የተፈጸመባት ሴትም በሲዎል የህክምና እርዳታ እየተደረገላት ነው፡፡

የኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ባለስልጣኑ ጥፋተኛ መሆናቸው ከተረጋገጠ ከፍተኛ ቅጣት ይጠብቃቸዋል፡፡

ለደህንነታቸው ሲባል ሚኒሰቴሩ ስማቸውን ይፋ ከማድረግ ተቆጥቧል፡፡

ምንጭ፡http://www.koreaherald.com/view.php?ud=20170712000845

 

Advertisement