ፈረንሳይ በ 2040 ሁሉንም ነዳጅ የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎችን እንደምታስወግድ አስታወቀች፡፡

ፈረንሣይ በ2040 ማለትም በ 23 ዓመት ውስጥ ሁሉንም የነዳጅ ተጠቃሚ ተሸከርካሪዎች ከአውራ ጎዳናዎቿ ውጭ ልታደርግ ማቀዷን አስታውቃለች ፡፡

የፓሪስ አየር ንብረት ሚኒስቴር ሚኒስትር ኒኮላ ሆሎት በፓሪስ ስምምነት መሠረት የአገሪቱ ብሔራዊ ግዴታዎችን ለመፈጸም የአምስት ዓመት ዕቅድ መውጣቱን ተናግረዋል፡፡


አዲሱ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በ2050 ሃገሪቱን ከበካይ ጋዝ ልቀት ነጻ ለማድረግ እየሰሩ ነው፡፡


ለዚህ እቅድ መሳካት ደግሞ የስዊድን የመኪና አምራች ቮልቮ ትልቁን ሚና የሚጫወት ሲሆን እ.ኤ.አ ከ 2019 በኋላ ኤሌክትሪክን የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎችን ብቻ ለማምረት እቅድ መያዙ ታውቋል፡፡ 
እቅዱ በፈረንሳይ የመኪና አምራቾች ላይ ጫና ፈጥሯል፡፡ ነገር ግን ይህን ቃል ለመፈፀም የሚያስችሉ ኘሮጀክቶች እየተከናወኑ ነው፡፡ በፈረንሳይ ድሆች የሚጠቀሙትን በካይ ቁሳቁስ ለመቀነስ አማራጭ የማቅረብ ስራም እየተሰራ ነው፡፡

ፈረንሳይ በ 2022 ዜጎች ከከሰል ሃይል ወጥተው ሌሎች የኤሌክትሪክ አማራጮችን እንዲጠቀሙ ለማስቻል 4 ቢሊዮን ዩሮ ወጭ በማድረግ እና የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦትን በማሳደግ የኃይል ማመንጫውን እንዲጠቀሙ እተሰራ ነው፡፡

ፈረንሳይ የኑክሌር ኃይልን እ.ኤ.አ. 2025 ከ 75 በመቶ ወደ 50 በመቶ ለመቀነስ እየሰራችም ነው፡፡ 
ፈረንሳይ ከአየር ብክለት ንፁህ አካባቢን ለመፍጠር እየሰሩ ካሉ ሃገራት ተርታ የተመደበች ሲሆን ከዚህ ቀደም ኔዘርላንድ እና ኖርወይ በ 2025 ጀርመን እና ህንድ በ2030 ከአየር ብክለት ንፁህ አካባቢን ለመፍጠር እየሰሩ ያሉ ሃገራት ናቸው፡፡

ምንጭ፡ኒዮርክ ታይምስ

 

 

Advertisement