በሃገረ ህንድ ነው ባለፈው ቅዳሜ አሾክ ኩመር የተባሉ የስድሳ ዓመት ኣዛውንት አመሻሽተው አልኮል ቢጤም ቀማምስው ወደ ቤት ይገባሉ፡፡
ሱናይና የተባሉት ባለቤታቸው በሁኔታው ደተኛ አልነበሩም፡፡
በንግግር መሃል ሃይለ ቃል ይነጋገሩና ሚሰት ወደ ማብሰያ ክፍል እራት ለማቅረብ ይገባሉ፡፡
በዚህ ማሃል ባል እራቴ ዘገየብኝ በሚል ምክንያት የ55 ዓመት እድሜ ያላቸውን ሚስታቸውን ተኩሰው ገድለዋል፡፡
ሟች አፋጣኝ የህክምና እርዳታ ቢደረግላቸውም ሊተርፉ አልቻሉም፡፡
ባል በድርጊታቸው መጸጸታቸውን ለፖሊስ ገልጠዋል፡፡
ምንጭ-ቢቢሲ