ዳሎል የሰው ልጅ በሌላ አለም ለመኖር ለሚያደረገው ጥረት የሚረዳ ነው ተባለ።

 

ተመራማሪዎች በኢትዮጵያ ሰሜን ምስራቅ የሚገኝው ዳሎል የሰው ልጅ በማርስ ላይ ለመኖር ለሚያደርገው ጥናት ከፍተኛ አስተዋጽዎ ያደርጋል ብለዋል።

የአሜሪካ ተመራማሪዎች እንዳሉት አከባቢው ካለው አደገኛ የአየር ሁኔታ ጋር በተያያዘ የሰው ልጅ በማርስ ላይ እንዴት መኖር እንደሚችል የሙከራ ስራዎችን ለማድረግ ያግዛል።

የዳሎል አማካኝ የሙቀት መጠን 35 ዲግሪ ሼሊሺየስ ቢሆንም አልፎ አልፎ እስከ 50  ዲግሪ ሼሊሺየስ ይደርሳል

በናሳ የተነሱ የሳተላይት ምስሎችም ይፋ ሆነዋል። 

ተመራማሪዎቹ የሰው ልጅ በዳሎል መኖሩም እንደ ተአምር የሚቆጠር ነው ብልዋል፡፡

ምንጭ: CNN

Advertisement